REPORT/DOCUMENTS

ETHIOPIAN HUMAN RIGHTS LAW SERIES VOL. XII (2020)

Ethiopian Human Rights Law Series Vol. XII (2020) Read More Download

NATIONAL IMPLEMENTATION PLAN FOR ADMINISTRATIVE PROCEDURE LAW

Draft National Implementation Plan for Administrative Procedure Law of Federal Republic of Ethiopia Read More Download

የሁለተኛ ዓመት የሥራ ክንዉን ዘገባ

አማካሪ ጉባዔዉ ተግባሩን በሚገባ መወጣት ይችል ዘንድ የለት ከዕለት የአስተዳደር ሥራ የሚያከናዉን ጽሕፈት ቤት ያቋቋመ ሲሆን፤ የሕግና ፍትህ ጉዳዮችን የሚመለከቱ ቴክኒካዊ ስራዎቹን የሚያከናውኑ የሥራ ቡድኖችንም መስርቷል። እያንዳንዱ የሥራ ቡድን በተለያዩ ሕጎችና አሰራሮች ላይ ጥልቅ ጥናት በማድረግ የማሻሻያ ሀሳቦችንና ረቂቅ ህጎችን ለመንግስት ያቀርባል። አማካሪ ጉባዔው እና ያቋቋማቸው የሥራ ቡድኖች በትምህርት ደረጃቸው የላቀ ደረጃ ላይ የደረሱና በሙያቸው አንቱ የተባሉ የሕግ፣ የሰቪል ማህበረሰብ፣ የመገናኛ ብዙሃን፣ የሰብዓዊ መብት እና የዲሞክራሲ ዘርፍ ባለሙያዎችን ያካተቱ ናቸው። እነዚህ ባለሙያዎች በዋናነት በበጎ ፈቃደኝነት የሚያገለግሉ በመሆኑ አገሪቷ የሚያስፈልጓትን የሕግና የፍትህ መዋቅር ማሻሻያዎች ያለ ክፍያና በከፍተኛ ሙያዊነት፣ ብቃትና ውጤታማነት እንድታከናውን ከፍተኛ ሚና እየተጫወቱ ይገኛል። Read More Download


COVID GUIDELINE

COVID-19 GUIDELINE Introduction This document has been prepared by the Secretariat of Legal and Justice Affairs Advisory Council, with input from the Ministry of Health, World Health Organization, and also take into account experiences of International Organizations. This COVID-19 guideline includes the measures to be taken at the Legal and Justice Affairs Advisory Council to work effectively during this pandemic. It provides key information for meeting organizers (secretariat employees and working groups’ leaders), members of Advisory Council, Consultants and Volunteers, how they should work and organize meetings/public consultations in the current situation. Therefore, you are kindly requested to follow all these rules diligently, to sustain a healthy and safe workplace or meeting room in this challenging environment. Everyone is also expected to respond responsibly to these health precautions. Read More Download

መመሪያ ቁጥር 24/2010

የፌደራል ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ በአዋጅ ቁጥር 943/2008 አንቀፅ 8/2/ሰ/ መሰረት ይህንን የፌዴራል ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ የሕግና ፍትሕ ጉዳዮች አማካሪ ጉባኤ ማቋቋሚያ መመሪያ ያወጣው የፍትሕና የዴሞክራሲ ተቋማትን የማሻሻል ሂደት ህዝብንና ባለሙያዎችን ባሳተፈ መልኩ ተግበራዊ ማድረግ አስፈላጊ በመሆኑ፤ የፍትህና ዴሞክራሲ ተቋማት አገልግሎት ውጤታማነትና የሕዝብ ፍላጎትን በማርካት ረገድ ያሉትን ፕሮግራሞች መተግበር አስፈላጊ በመሆኑ እና ተቋማዊ የለውጥ ፕሮግራሞችን መንደፍና አፈጻጸማቸውን መገምገም፤ መረጃን እና ልምድን አሳታፊና ሳይንሳዊ በሆነ መንገድ መሰብሰብና መተንተን አስፈላጊ መሆኑን በማመን ነው:: መመሪያው የሕግና ፍትሕ ጉዳዮች አማካሪ ጉባኤን ዓላማ፣ ስልጣን እና ተግባር የሚዘረዝር ሲሆን ጉባኤው በፌዴራል ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ ስር የተቋቋመ እና ተጠሪነቱ ለጠቅላይ ዓቃቤ መሆኑን ይገልጻል፡፡ በተጨማሪም የጉባኤው ዓላማ በሕግና ፍትሕ ጉዳዮች ዙሪያ መረጃና ጥናትን መሰረት በማድረግ ለፌዴራል ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ ሙያዊ ምክር መስጠት፣ በፌዴራል ጠቅላይ ዓቃቤ ህግ የሚረቀቁ ህጎች ጥራታቸውን የጠበቁ እንዲሆኑ ተገቢውን እገዛ ማድረግ፣ የህግና የፍትህ ስርአት ማሻሻያ ፕሮግራም ውጤታማ በሆነ መንገድ እንዲከናወን አቅጣጫዎችን እና የመፍትሄ ሀሳቦችን ማመንጨት መሆኑን መመሪያው ይገልጻል፡፡ በመመሪያው ከተቀመጡት የጉባኤው ስልጣንና ተግባራት መካከል የሚከተሉት ዋነኞቹ ናቸው፡፡ ጉባኤው በህግና ፍትህ ጉዳዮች ላይ መሻሻል ያለባቸውን ተቋማት፣ አሰራሮችና ህጎች በሚመለከት የፌዴራል ጠቅላይ ዓቃቤ ህግን ያማክራል፣ የፍትሕና ዴሞክራሲ ተቋማት ፍትሃዊ፣ ቀልጣፋ፣ ውጤታማ፣ ህዝብን የሚያረካ አገልግሎት እየሰጡ መሆኑን ለመከታተልና ለመገምገም የክትትልና ግምገማ ማዕቀፍ ያዘጋጃል፤ የክትትልና የግምገማ ማዕቀፈን፣ መረጃና ጥናትን መሰረት በማድረግ የተለያዩ የፍትህና ዴሞክራሲ ተቋማት የሚሰጧቸው አገልግሎቶች ያሉበትን ወቅታዊ ሁኔታና ችግሮችን ይለያል፣ የመፍትሄ ሃሳቦችን እና ረቂቅ ህጎችን ለፌዴራል ጠቅላይ ዓቃቤ ህግ ያቀርባል፤ የምክክርና ዉይይት መድረኮች ያዘጋጃል፣ ይመራል፡፡ Read More Download

የህግና ፍትህ ጉዳዮች አማካሪ ጉባኤ የስነ-ስርዐት ደንብ

ይህ ደንብ የወጣው የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ መንግስት ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ በተቋቋመበት አዋጅ ቁጥር 943/2008 አንቀጽ 8(2)(ሰ)፣ መመሪያ ቁጥር 1/2010 መሰረት የተቋቋመው የህግና ፍትህ ጉዳዮች አማካሪ ጉባኤ ስራውን በአግባቡ ለማከናወንና የተጣለበትን ኃላፊነት በብቃት ለማከናወን የሚያስችለው የአሰራር ሥነ ሥርዓት ደንብ የሚያስፈልገው በመሆኑ ነው፡፡ ደንቡ የጉባኤው ሰብሳቢና ምክትል ሰብሳቢ በጉባኤው አባላት የሚመረጡ መሆኑን፣ ለሰብሳቢነትና ለምክትል ሰብሳቢነት ለየብቻው ከጉባኤው አባላት መሀል ሁለት፣ ሁለት፣ እጩዎች ቀርበው ከፍተኛውን ድምፅ ያገኘው ዕጩ ኃላፊነቱን የሚረከብ መሆኑን እና ምርጫው የሚከናወነው በምስጢር ድምፅ አሰጣጥ ስርዓት መሰረት መሆኑን ይገልጻል፡፡ የጉባኤውን የስብሰባ ሥርዓት በሚመለከት ምልዓተ ጉባኤው የሚኖረው ከጉባኤው አባላት መሀል ሰባት አባላት ሲገኙ መሆኑን፣ በጉባኤው ስብሰባ ላይ ምልዓተ ጉባኤ ኖሮ ሰብሳቢውና ምክትል ሰብሳቢው ካልተገኙ ስብሰባው በዕለቱ በሚመረጥ የጉባኤው አባል የሚመራ መሆኑን ደንቡ ይገልጻል፡፡ በተጨማሪም የጉባኤው ጽ/ቤት በጠቅላይ ዐቃቤ ህግ በሚመደብ ኃላፊ የሚመራ መሆኑን፣ ጽ/ቤቱ የጉባኤውን ዝርዝር የዕለት ተዕለት ስራዎች የሚያከናውን አስፈፃሚ አካል መሆኑን፣ የመንግስት ሰራተኞችን የሚመለከቱ አግባብ ያላቸው ህግጋትና ደንቦች እንደተጠበቁ ሆኖ የጉባኤውን ስራ በተመለከተ የጽ/ቤቱ ሃላፊ ተጠሪነት ለጉባኤው ሰብሳቢ መሆኑን፣ ጽሕፈት ቤቱ በጉባዔው የቀረቡለትን የስራ መመሪያዎች ለመፈጸም በሚያችለው መልኩ የሚያደራጅ መሆኑን፣ ለዚህም የጥናትና አርቃቂ ቡድኖች የሚያደራጅ መሆኑን፣ የቡድኑ አባላት ከጽህፈት ቤቱ ሰራተኞችና ከጽሕፈት ቤቱ ውጭ ያሉ ተከፋይና የበጎ ፈቃድ አማካሪዎችን የሚያካትት መሆኑን እና ጽሕፈት ቤቱ ለእነዚህ ቡድኖች ግልጽ የስራ ሃላፊነትና ድርሻ በጽሁፍ የሚሰጥ መሆኑን ደንቡ ያትታል፡፡ Read More Download

ROAD MAP OF THE JUSTICE AND LEGAL AFFAIRS ADVISORY COUNCIL

First Year: - This Roadmap is expected to guide the activities of the AC and its Secretariat discharge their mandate in relation to the seven sub-programs of the reform package. Taking in to account the need for prioritization, the proposal in this road map is that in the first year of its mandate, i.e. in 2011 Ethiopian calendar, the AC will focus on primary legislations and institutional changes in the following five subprograms; ● The Law-Making Process ● The Judicial System ● The Criminal Justice System ● The Civil and Administrative Justice System ● Democratic Institutions. Second and Third Year: - The above timeline means that follow up and support in the implementation of the reform proposals of the AC as well as work on the Legal Education and Training sub-program and Legal and Related Services sub-program (with the exception of the review concerning the regulation of the legal profession regarding, which a lot of work has already been done) will be the focus on the AC in the last two years of its mandate, i.e. 2012-2013 Ethiopian calendar. From the Civil and Administrative Justice System, the focus on the first year would also largely be on the Administrative, i.e. the regulatory policy and enforcement component of the sub-program. Follow up and support by the AC and its secretariat would include; tracking the extent to which its recommendations have been adopted and implemented, drafting secondary legislation and manuals needed to ensure the effective implementation of the AC’s recommendations, evaluating and monitoring the impact of its recommendations, and the provision of training intended to facilitate the effective implementation of the AC’s recommendations. Generally speaking, as the first year of its mandate ends, the AC will partially shift its attention to providing institutionalized support to enhance the extent to which its recommendations are put into practice. Read More Download

የሕግ ማሻሻያ የስራ ክንዉን አጭር ዘገባ

የኢ.ፌ.ድ.ሪ ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ሀገራችን ያለችበትን የለውጥ ሂደት ውጤታማነት ለማረጋገጥ የተለያዩ የተቋማትና የሕግ ማሻሻያ ስራዎችን እየሠራ እንደሚገኝ ይታወቃል፡፡ የነዚህ ማሻሻያ ስራዎች ዓላማ ለውጡ ተቋዋማዊ፣ ሁሉን አቀፍና በጥናት በተደገፈ አካሄድ ተግባራዊ ተደርጐ የሕግ የበላይነትና ፍትህ የሠፈነባት፣ ሰብዓዊ መብቶች የተከበሩባት እና በዲሞክራሲያዊ አግባብ የምትመራ ሃገር መገንባት ነው፡፡ ይህን አላማ ለማሳካት የኢ.ፌ.ድ.ሪ ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ከፍተኛ ልምድና ብቃት ያላቸውን አስራ ሶስት የሕግ ባለሞያዎች ያቀፈ “የሕግና ፍትህ ጉዳዮች አማሪ ጉባዔ” አቋቁሟል፡፡ ይህንን ጉባዔ ለመደገፍ ሥራውንም ለማሳለጥ የጉባዔው ፅህፈት ቤት ተቋቁሞ ባለሞያዎችም ተቀጥረዋል፡፡ አማካሪ ጉባዔው ከመቋቋሚያ መመሪያው በተጨማሪ የሚመራበትን ውስጠ ደንብ አፅድቆ ተግባራዊ አድርጓል፡፡ በተጨማሪም ጉባኤው የማሻሻያ ሥራውን የሚመራበት እና አጠቃላይ አላማውንና የትኩረት አቅጣጫውን የሚያሳይ ፍኖተ ካርታ አዘጋጅቶ አፅድቋል፡፡ እንዲሁም በጉባዔውና በጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ተግባራዊ በሚደረጉ የማሻሻያ ሥራዎች የባለድርሻ አካላትና የህዝብ ተሳትፎን ለማረጋገጥ የሚረዳ የህዝብ ተሳትፎ ስትራቴጂ ሰነድ ተዘጋጅቶ በስራ ላይ ውሏል፡፡ አማካሪ ጉባኤው ያቋቋመው የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች የሕግ ማዕቀፍ የሥራ ቡድን፣ አሁን በሥራ ላይ ያለውን “የበጐ አድራጐቶችና የማህበራት አዋጅ”፣ እንዲሁም የአዋጁን አተገባበርና ተያያዥ ጉዳዮችን የሚዳስስ ጥናት አካሄዶ፤ በጥናቱ ግኝት መሠረት ባቀረበው ምክረ ሃሳብ አዲስ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ሕግ ረቂቅ ተዘጋጀቶ፣ ረቂቁ ለሚኒስትሮች ምክር ተመርቷል፡፡ ረቂቅ አዋጁ ለሚኒስትሮች ምክር ቤት ቀርቦ የጸደቀ ሲሆን በቅርቡ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ፀድቆ በስራ ላይ ይውላል ተብሎ ይጠበቃል፡፡ በአማካሪ ጉባዔውና በጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ የተቋቋመው የዲሞክራሲ ተቋማት የስራ ቡድን በቅድሚያ ለምርጫና ተያያዥ ጉዳዮች አትኩሮት በመስጠት የተለያዩ ተግባራትን እያከናወነ ይገኛል፡፡ ፀረ-ሽብር ህጉን ይዘትና አተገባበር ለማጥናት የተቋቋመው የሥራ ቡድን የፀረ ሽብርተኝነት አዋጁንና አዋጁ በስራ ላይ የዋለበትን መንገድ የሚገመግም ጥናት አካሄዶ፣ በጥናቱ ላይ በመመስረት ረቂቅ አዋጅ ያዘጋጀ ሲሆን ረቂቅአዋጁን የአማካሪ ጉባኤው በመገምገም ላይ ይገኛል፡፡ የሚዲያ ሕጐችን ለማሻሻል የተቋቋመው የጥናት ቡድን የኢትዮጵያን የሚዲያ ዘርፍ የህግ ማዕቀፍ የሚዳስስና ችግሮቹን የሚለይ ጥናት አካሄዶ በማጠናቀቅ የባለድርሻ አካላት የምክክር መድረኮች ካገኘው ግብዓት በመነሳት የሕግ ማርቀቅ ሥራ የጀመረ ሲሆን በጥቂት ወራት ውስጥ የሥራ ቡድኑ የሚዲያ የሕግ ማዕቀፉን የሚያሻሽሉ ረቂቅ አዋጆችን አዘጋጅቶ ለአማካሪ ጉባኤውና ለመንግስት እንደሚያስረክብ ይጠበቃል፡፡ በተጨማሪም ለረጅም ጊዜ በሥራ ላይ የቆየውን የንግድ ሕግ ለማሻሻል ከዚህ ቀደም የተጀመረው ሥራ በቅርቡ ተጠናቆ ረቂቅ የንግድ ህግ የተዘጋጀ ቢሆንም ይህን አይነት ሕግ ለሃገሪቱ ያለውን ኢኮኖሚያዊ ፋይዳ፣ በኮድ መልክ የሚዘጋጁ ህጐች ሊኖራቸው የሚገባውን ዘመን ተሻጋሪ ባህሪና የንግድ እንቅስቃሴ በአሁኑ ወቅት ከመቼውም ጊዜ በላይ ድንበር ተሻጋሪ እየሆነ መምጣቱን ከግምት ባስገባ መልኩ ረቂቁን መከለስና ማሻሻል አስፈላጊ ሆኖ ተገኝቷል፡፡ Read More Download

YEAR I ACTIVITIES REPORT

The Legal and Justice Affairs Advisory Council (LJAAC, the Advisory Council) was established by the Attorney General’s Office (AGO) of the Federal Democratic Republic of Ethiopia (FDRE) on 29 June 2018. Composed of 13 prominent legal professionals, the Advisory Council is mandated with advising the Attorney General’s Office in matters relating to the reform of the legal and justice system in a way that is compatible with constitutional principles relating to human rights, democracy and the rule of law. More specifically, the Advisory Council’s mandate and role include: - undertaking a rigorous assessment of laws, institutions, and practices affecting the efficiency and effectiveness of justice and democratic governance institutions; - identifying/analyzing/collating the key challenges encountered in realizing an accountable public administration system, rule of law and full implementation of constitutionally guaranteed rights; and - proposing to the Office of the Attorney General methodically researched, pragmatic and programmatic reform packages that address the legal and institutional shortcomings. In order to accomplish its mandate, the Advisory Council commenced by staffing a Secretariat and Technical Working Groups (WGs) composed of volunteer legal and other prominent professionals from different sectors, who would undertake research on these laws and propose recommendations for amendment. It also staffed a Secretariat with technical staff to lead on providing technical and administrative support to the working groups and the Council. In addition to describing the work of the Advisory Council and its different bodies, this report illustrates their achievements, plans, and current and expected challenges. The objective of the LJAAC is to effectively advise the government of Ethiopia in its effort to advance the cause of justice, uphold the rule of law, protect human rights and build a genuinely democratic federal system of governance. The Secretariat, also established by Directive No. 24/2010, is the Advisory Council’s administrative arm. It is responsible for planning, administering and implementing the Advisory Council’s mandate in addition to liaising between the Advisory Council and the Attorney General’s Office. In the early stages of its inception the work of the 'Advisory Council' focused on establishing a functional structure, staffing that structure with competent personnel, preparing a roadmap for its work, and launching the activities of the WGs, the Secretariat and the Council itself. With the Secretariat and members of the Advisory Council taking the initiative, the Council: - Recruited members of the WGs and Secretariat and continue to do so as the need arises; - Reviewed and evaluated Inception Reports from each of the WGs; - Established an online voting system for the Advisory Council; - Prepared and endorsed a Working Group Code of Conduct; - Prepared and endorsed the Rules of Procedure of the Advisory Council; - Prepared and endorsed a Public Consultation Strategy; - Developed the Secretariat’s Diversity and Inclusion Policy; - Developed the Secretariat’s Non-Disclosure Policy; - Secured funding and/or other forms of cooperation and support from international institutions; - Where the need arose, recruited and hired subject area experts both locally and internationally with the support of funding and partner institutions; With the establishment and staffing of the WGs, the LJAAC saw an exponential expansion of its capacity deploying 143 long-term volunteers, 8 fulltime staff, and 13 (local and foreign) short term consultants. While its staffing activities were ongoing, the LJAAC set out to achieve the first year of its mandate (i.e. in 2011 Ethiopian calendar), which prioritized normative and institutional frameworks without which the country’s pro-democracy and pro-rights course could be hampered. In accordance with its plans, the Advisory Council focused on primary legislation and institutional changes in the Law-Making Process, Judicial System, Criminal Justice System, Civil, and Administrative Justice System, and Democratic Institutions Sub-Programs. The major milestones achieved by the Advisory Council and its roadmap for the remainders of the first year of its plan are outlined in the following sub-section. Read More Download

WORK PLAN FOR YEAR II

The work of the LJAAC in the second year of the project will be composed of three major categories: the winding down of Year I activities that were either not completed due to different contingencies; setting up a mechanism through which it ensures, or at least supports the effectiveness and sustainability of the country’s reform efforts; and the undertaking of new activities that fall into its mandate. In its second year of activities, the LJAAC will also, make a concerted effort to tackle the challenges of legal and justice reform by taking stock of its own and previous experiences. The LJAAC will thus support the implementation process by taking stock of previous, current and comparative experiences, monitoring the implementation of new legislation, and designing a system that will provide metrics through which the government of Ethiopia can measure the effectiveness of the reforms. The activity will specifically include the monitoring of the implementation of the laws drafted by the Civil Society, the Media Law, Anti-Terrorism Proclamation, Democratic Institutions, Administrative Law, Criminal Procedure and Legal Practice WGs. The work under this category includes evaluating the extent to which its recommendations have been adopted and implemented, monitoring the impact of its recommendations and its work in general, pursuing avenues to ensure the reform process is achieving its goals, and providing institutionalized support for implementing bodies. The AC has determined that the primary onus for implementing the reform work rests on sector administrators or institutions responsible for implementing the legal and other reforms coming out of the AC’s work. Requiring such institutions to take the lead is not only legally mandated but such an arrangement allows these sector administrators the opportunity to develop long-term capacity that will be needed to ensure that the durability of the impact of the reform work. However, it is also imperative on the LJAAC to provide support to this process as an independent advisory body which has played a principal role in carrying out the legislative reform and has the mandate to monitor their practical implementation. In addition, unlike sector administrators with institutional memories and a workforce that has been implementing the infamous/repealed legislation, the LJAAC can play a role in ensuring that the legal reform has a greater impact on their implementation and practice. Accordingly, the AC’s implementation-support, monitoring, and evaluation work, which applies to Year I, II, and III processes, will include: • preparing implementation-modules which broadly set out the regulatory framework required for the implementation of new laws; • developing metrics that measure the success of the reform both in terms of the specific reformed sector and in relation to other sectors; • identifying (re)training, legal literacy, communication, civic engagement, curriculum review, automation, and other needs; • monitoring the practical results of its work in collaboration with the AGO and sector administrators or institutions responsible for implementing the legal and other reforms coming out of the AC’s work; • supporting the drafting of subsidiary legislation, training manuals and employee manuals as needed to ensure the effective implementation of the AC’s recommendations; • organizing and implementing training intended to facilitate the effective implementation of the AC’s recommendations; • conducting legal literacy projects to ensure the engagement and support of the public with the reform process and as part of the AC’s public outreach efforts; • conducting a curriculum review project in collaboration with the Min of Higher xxx and conduct law school and professional conferences and seminars to provide subject-area professionals/lecturers and law students/graduates opportunities to be up to date with developments. Substantively and temporally mapping out this task in detail is challenging due to the involvement of the HoPR and numerous sector administrators in the timeline and implementation of the reform work. Because of this, the LJAAC will only plan out parts of the work which are clearly inside its ambit and offer to sector administrators its support in implementing the relevant laws. The AC will keep intact the original WG that drafted the relevant laws to provide it with technical support in its implementation-support, monitoring, and evaluation activities. Read More Download

የአንደኛ ዓመት የስራ ክንውን ሪፖርት

የኢ.ፌ.ድ.ሪ ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ሀገራችን ያለችበትን የለውጥ ሂደት ውጤታማነት ለማረጋገጥ የተለያዩ የተቋማትና የሕግ ማሻሻያ ስራዎችን እየሠራ እንደሚገኝ ይታወቃል፡፡ የነዚህ ማሻሻያ ስራዎች ዓላማ ለውጡ ተቋዋማዊ፣ ሁሉን አቀፍና በጥናት በተደገፈ አካሄድ ተግባራዊ ተደርጐ የሕግ በላይነትና ፍትህ የሠፈነባት፣ ሰብዓዊ መብቶች የተከበሩባት፣ በዲሞክራሲያዊ አግባብ የምትመራ ሀገር መገንባት ነው፡፡ ይህን ዓላማ ለማሳካት የኢ.ፌ.ድ.ሪ ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ከፍተኛ ልምድና ብቃት ያላቸውን አስራ ሶስት የሕግ ባለሞያዎች ያቀፈ “የሕግና ፍትህ ጉዳዮች አማሪ ጉባዔ” አቋቁሟል፡፡ አማካሪ ጉባዔዉ የሰብዓዊና ዴሞክራሲ መብቶችን እንዲሁም የሕግ የበላይነትን የመሳሰሉ ሕገ-መንግስታዊ መርሆዋች መሰረት በማድረግ ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግን በሕግና ፍትሕ ማሻሻያ ጉዳዮች ላይ የማማከር ስልጣን የተሰጠዉ ሲሆን የአማካሪ ጉባዔዉ ስልጣንና ተግባራት በዋናነት የሚከተሉትን ያጠቃልላል፡- • በዴሞክራሲያዊ አስተዳደር ተቋማት ዉጤታማነት ላይ ተፅዕኖ ባላቸዉ ሕጎች፣ ተቋማትና አሰራሮች ላይ ጥልቅ የሆነ ጥናትና ግምገማ ማድረግ፤ • ተጠያቂነት የሰፈነበት የመንግስት አስተዳደር ለማስፈን፣ የሕግ የበላይነትን ለማረጋገጥና ሕገ- መንግስታዊ መብቶችን ሙሉ በሙሉ ለማረጋገጥ በሚደረገዉ ጥረት ያጋጠሙ ተግዳሮቶችን መለየት፣ ማጥናትና መሰብሰብ፤ • ሕጋዊና ተቋማዊ ችግሮችን ሊፈቱ የሚችሉ አይነታዊ(ገላጭ) የጥናት ውጤቶች ላይ መሠረት ያደረጉ የማሻሻያ ሀሳቦችን የተጠኑና በፕሮግራም የተደገፉ እዉነታ ላይ የተመሰረቱ የማሻሻያ ፓኬጆችን ለጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ማቅረብ፡፡ አማካሪ ጉባዔዉ ስልጣንና ተግባሩን በሚገባ መወጣት ይችል ዘንድ የለት ከዕለት የአስተዳደር ስራ የሚያከናዉን የአማካሪ ጉባዔ ፅህፈት ቤት፣ በጎ ፈቃደኞችን እና ቋሚ ባለሙያዋችን ያካተተ የስራ ቡድኖች አቋቁሟል፡፡ የጉባዔዉ ጽ/ቤት አስተዳደራዊና የቴክኒክ ድጋፎችን ለስራ ቡድኖችና ለጉባዔዉ የሚሰጥ ሲሆን እያንዳንዱ የስራ ቡድን በተለያዩ ሕጎች ላይ ጥልቅ ጥናት በማድረግ የማሻሻያ ሀሳቦችን ያቀርባል፡፡ ይህ ዓመታዊ ሪፖርት በፕሮግራሙ አንደኛ ዓመት ዉስጥ በአማካሪ ጉባኤዉና በስሩ ባሉት የጉባኤዉ ጽ/ቤት እና የስራ ቡድኖች የተከናወኑ ስራዋችንና ያጋጠሙ ተግዳሮቶችን በማካተት እንደሚከተለዉ ቀርቧል፡፡ የሕግና ፍትሕ ጉዳዮች አማካሪ ጉባዔ ዋና ዓላማ የኢትዮጵያ መንግስት ፍትሕን ለማሻሻል፣ የሕግ የበላይነትን ለማስከበር፣ ሰብዓዊ መብቶችን ለመጠበቅና እዉነተኛ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሀገር ለመገንባት የሚያደርገዉን ጥረት ዉጤታማ በሆነ መልኩ ማማከር ነዉ፡፡ የሕግና ፍትሕ ጉዳዮች አማካሪ ጉባዔዉ በመጀመሪያው የስራ ዘመን የስራ ትግበራ መዋቅር መዘርጋት፣ መዋቅሩን በተወዳዳሪ ሰራተኞች ማደራጀት፣ ፍኖተ ካርታ ማዘጋጀት፣ የስራ ቡድኖችን ማዋቀር፣ የጽ/ቤቱን እነዲሁም የጉባዔዉን ስራ የማስጀመር ተግባራት ላይ ትኩረት ሰጥቶ ሰርቷል፡፡ በጉባዔዉ እና በጽ/ቤትና ተነሳሽነት የሚከተሉትን ተግባራት ተከናዉኗል፡- · የስራ ቡድኖችንና የጽ/ቤቱን አባላት የመለመለ ሲሆን በቀጣይም እንዳስፈላጊነቱ ተመሳሳይ ስራ ያከናዉናል፣ · የጥናት ቡድኖችን የስራ አጀማመር ሪፖርት ተቀብሎ ገምግሟል፣ · ለአማካሪ ጉባዔዉ የቀጥታ ድምፅ መስጫ ስዐርት ዘርግቷል፣ የስራ ቡድኖች የሥነ-ምግባር ደንብ በማዘጋጀት አፅድቋል፣ · አማካሪ ጉባዔው የሚመራበትን ውስጠ ደንብ አፅድቆ ተግባራዊ አድርጓል፣ በተጨማሪም ጉባዔው የማሻሻያ ሥራውን የሚመራበት፣ አጠቃላይ ዓላማውንና የትኩረት አቅጣጫውን የሚያሳይ ፍኖተ ካርታ አዘጋጅቶ አፅድቋል፣ · የህዝብ ተሳትፎ ስትራቴጂ ስነድ ተዘጋጅቶ በስራ ላይ ውሏል፣ · የጉባዔዉ ጽ/ቤት የብዝሃነትና አካታችነት ፖሊሲ አዘጋጅቷል፣ · የጉባዔዉ ጽ/ቤት ሚስጥር ጠባቂነትና መረጃ ያለማዉጣት ፖሊሲ አዘጋጅቷል፣ · የገንዘብ ድጋፍና ወይም ሌሎች ትብብሮችን ዓለማቀፍ ተቋማት አግኝቷል፣ · አስፈላጊ በሆነ ጊዜ በገንዘብ ድጋፍና በአጋር ድርጅቶች ትብብር በመታገዝ በየዘርፉ የሀገር ዉስጥና ዓለም አቀፍ ባለሙያዋችን ቀጥሯል፡፡ የስራ ቡድኖች መቋቋማቸዉን ተከትሎ የአማካሪ ጉባዔዉ አቅም በከፍተኛ ሁኔታ ጨምሯል፡፡ ይኸዉም 143(አንድ መቶ አርባ ሦስት) የረጅም ጊዜ በጎ ፈቃደኞች፣ 8(ስምንት) የሙሉ ጊዜ ተቀጣሪዎች፣ 13(አስራ ሦሥት) የሀገር ዉስጥና የዉጭ የአጭር ጊዜ አማካሪዎች በአማካሪ ጉባዔዉ ስር እየሰሩ ይገኛሉ፡፡ ተቋሙን በሰዉ ኃይል የማደራጀት ስራዉ እንደቀጠለ ሲሆን አማካሪ ጉባዔዉ በመጀመሪያ ዓመት የስራ ዘመኑ(በኢትዮጵያ አቆጣጠር 2011 ዓ/ም) ያለጉባዔዉ ተሳትፎ የማይታሰቡ ሕጋዊና ተቋማዊ ለዉጦችን ለማሳካት ተቃርቧል፡፡ በዕቅዱ መሠረት አማካሪ ጉባዔዉ ከሕግ ማውጣት ሂደት፣ ከፍትሕ ሥርዓት፣ ከወንጀል ፍትሕ ሥርዓት፣ ከፍትሐብሔርና አስተዳደር ሕግ ፍትሕ ሥርዓት እና ከዴሞክራሲያዊ ተቋማት ንዑስ መርሀ-ግብሮች ላይ የመጀመሪያ ደረጃ ሕጎችን የማውጣትና ተቋማዊ ለውጥ ላይ ትኩረቱን አድርጎ ሰርቷል፡፡ Read More Download

የሁለተኛ ዓመት የሥራ ዕቅድ

የሕግ እና የፍትሕ ጉዳዮች አማካሪ ጉባዔ የሁለተኛ ዓመት የሥራ ዘመን ዕቅድ ሦስት ዋና ዋና ዘርፎችን የሚይዝ ይሆናል፡፡ አንደኛው በመጀመሪያው ዓመት የሥራ ዕቅድ ተይዘው የነበሩ እና በተለያየ ምክንያት መጠናቀቅ ያልቻሉ ስራዎችን ማጠናቀቅ ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ በአገሪቷ የተጀመሩ የፍትህ ማሻሻያ ስራዎችን ውጤታማነት እና ዘላቂነት ለማረጋገጥ ወይም ለመደገፍ የሚያስችሉ ስልቶችን መዘርጋት ነው፡፡ በመጨረሻም በአማካሪ ጉባዔው የሥራ ወሰን ስር ሊወድቁ የሚችሉ አዲስ ስራዎችን መስራት ይሆናል፡፡ አማካሪ ጉባዔው በሁለተኛው ዓመት የሥራ ዘመኑ ያጋጠሙ ችግሮችን እና የቀደሙ ልምዶችን ታሳቢ በማድረግ በፍትሕ ማሻሻያ ስራዎች ላይ የሚያጋጥሙ ተግዳሮቶችን ለመፍታት ጠንካራ እንቅስቃሴ የሚያደርግ ይሆናል፡፡ ይህም ከአለፈው ዓመት የተሸጋገረ የአማካሪ ጉባዔው ቁልፍ ተግባር እንደሚሆን ይጠበቃል፡፡ አንዳንዶቹ በመጀመሪያው የሥራ ዘመን በዕቅድ የተያዙ ስራዎች በተለያዩ ተገማች እና ድንገተኛ በሆኑ ምክንያቶች ወደ ሁለተኛዉ የሥራ ዘመን ሊሸጋገሩ እንደሚችሉ ይጠበቃል፡፡ ከነዚህ ስራዎች መካከል በጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ፣ በሚንስትሮች ምክር ቤት ወይም በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሕግ ማውጣት ስራዎች ሂደት ላይ ድጋፍ ከማድረግ ጋር የተያያዙ ተግባራትን ማጠናቀቅን በምሳሌነት መጥቀስ ይቻላል፡፡ የአማካሪ ጉባዔው የመጀመሪያው ዓመት የሥራ ዘመን እየተጠናቀቀ መሆኑን ተከትሎ አማካሪ ጉባዔዉ ትኩረቱን ለሰብዓዊ መብት፣ ዴሞክራሲ እና የሕግ የበላይነት መረጋገጥ አይነተኛ ሚና የሚያበረክቱ የማሻሻያ ፓኬጆች አፈጻጸም ወደ መደገፍና መመዘን ስራ የሚያዞር ይሆናል፡፡ ይህ የሆነበት ምክንያትም በአግባቡ የተቀረጹ ሕግጋት መኖር ብቻውን የለውጥ ስራውን ዋና ግብ ለማረጋገጥ በቂ አይሆንም ከሚል እሳቤ ነው፡፡ በመሆኑም የሕግና ፍትሕ ጉዳዮች አማካሪ ጉባዔ የአዳዲስ ሕጎችን ተግባራዊነት ለመደገፍ ቀደምት ፣ወቅታዊና ተነፃፃሪ ልምዶችን በመጠቀም የአፈጻጻም ሂደቱን ይደግፋል፤ እንዲሁም የኢትዮጲያ መንግስት የለውጡን ውጤታማነት ለመለካት የሚችልባቸውን አመልካቾች (መለኪያዎችን) ያካተተ ሥርዓት ቀርጾ ያቀርባል፡፡ ይህ ተግባር በሲቪል ማህበረሰቡ፣ በመገናኛ ብዙሃን ሕግ፣ በፀረ-ሽብር አዋጁ፣ በዴሞክራሲ ተቋማት፣ በአስተዳደር ሕጉ፣ በወንጀል ሥነ-ሥርዓት እና የሕግ ስራዎችን የሚሰሩ የሥራ ቡድኖች ያዘጋጇቸውን ሕጎች አፈጻጸም መገምገምን የሚያካትት ይሆናል፡፡ Read More Download

PUBLIC CONSULTATION POLICY

This document is intended to outline the justifications, guiding principles and modalities for the public for consideration by the Council. Once the document is considered and adopted by the Council, this document or a revised version would serve as the Public Consultation Policy of the Council. Public Consultation, for the purpose of this document, is understood to mean a process of soliciting the views, opinions, and input of interested and affected groups. This could be at any stage in the process of identifying problems with and evaluating existing laws, institutions, and procedures and developing solutions and interventions. Consultation is meant to be a process of seeking information with a view to enhancing the effectiveness and quality of the interventions and solutions to be proposed by the Council to the FDRE Attorney General/Government. The Council’s approach to public consultation shall be guided by the following principles; Inclusiveness: - the Council shall strive to ensure that it will employ tools of public consultation that will optimize the opportunity of all relevant stakeholders providing their input. In particular, the Council shall endeavor to solicit the views and input of marginalized and vulnerable members of society in its public consultation effort. Transparency: - the Council shall strive to provide the necessary information in a timely fashion to facilitate meaningful public consultation and participation with relevant stakeholders. Two Way Communication: - the Council shall give due weight and consideration to inputs it receives from the public through various modalities of public consultation. Instruments of public consultation should not only be used by the Council to provide information to the public about its work but, also to gather input from the public about issues falling within the mandate of the Council. · Efficiency: - the Council shall employ modalities of public consultation that would enable it to make the most efficient use of its time and resources. Given the urgent nature of the task at hand and the pressing demand of the public for reform in the justice sector, the Council should opt for the most expedient means of securing input from the public and relevant stakeholders. Read More Download

በሕግ ማርቀቅ ሂደት የሕዝባዊ ተሳትፎና ምክክር ፍኖተ-ካርታ

የሕዝባዊ ተሳትፎና ምክክር ጽንሰ ሃሳብና አሰራር የሚመነጨው ከነባር ሊበራል የውክልና ዲሞክራሲ (representative democracy) አተገባበር ላይ የታዩ ድክመቶችን ከማረም ጋር ከተያያዘ ሙከራ ነው። ከውክልና ዲሞክራሲ ስርዓት ዋና ድክመቶች አንዱ በተወሰነ ግዜ ብቻ የሚካሄዱ ምርጫዎች የመራጮችን ወይም ባጠቃላይ የሕዝቡን ፍላጎት በአግባቡ ማንጸባረቅ አለመቻላቸውና ተመራጮች በሁለት ምርጫዎች መሃል ባለው የጊዜ ክፍተት ለመራጩ ተጠያቂ ያለመሆን አዝማምያ ነው። በዚህና በተያያዥ ምክንያቶች የተነሳ በቁጥር አና ሳየሆኑ የየመደብ፣ የፖለቲካና ቢሮክራስያዊ ልሒቃን በዲሞክራሲያዊ አገዛዝ በማይጠበቅ ደረጃ አንዳንዴም ፀረ-ዲሞክራሲ በሆነ ሁኔታ የሃገሪቱን ሥልጣን ቁጥጥራቸው ስር የመዋል አዝማምያ ሊፈጥሩ ይችላሉ። የሕዝባዊ ተሳትፎና ምክክር የፖለቲካ ስርዓቶች ዲሞክራስያዊነትን ከማጠናከራቸው፣ከሰብዓዊና ዲሞክራስያዊ መብቶች መመንጨታቸውና ለብዙ መብቶች መከበርና መረጋገጥ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ከማድረጋቸው፣ ባለሙያዎች በቀላሉ ሊያውቋቸው የማይችሉ የረቂቅ ሕግና ፖሊሲዎች ማሕበራዊ ተጽዕኖዎችና የሕዝብ አስተያየቶችን የሚያመላክቱ ከመሆናቸው፣እናም ሕጎች ሕዝባዊ ተቀባይነት ኖሯቸው የሃገረ መንግስት አስገዳጅ ሃይል መጠቀም ሳያስፈልግ በውዴታ የሚፈጸሙበትን ሁኔታ ከማበረታታቸው፣እናም የመልካም አስተዳደር መለኪያ ከመሆናቸው አንጻር በሕግ ማርቀቅ ሂደት ውስጥ ሊተዉ የማይችሉ ያደርጋቸዋል። ሕዝባዊ ተሳትፎና ምክክር በሚወጡ ሕጎች ጥራትና ዲሞክራሲያዊነት ላይ ከሚኖራቸው አዎንታዊ አስተዋጽኦ በተጨማሪ ሕብረተሰቡ በፖለቲካ ስርዓቱ ላይ ያለውን አመኔታ ይጨምራሉ።ኢትዮጵያ በዴሞክራሲያዊ ስርዓት ግንባታ ሂደት መጀመርያ ላይ ከመሆኗ አንጻር ለሕዝባዊ ተሳትፎና ምክክር ልዩትኩረት ሊሰጣቸው ይገባል። በህግ ማርቀቅ ሂደት ውስጥ በተለይ በህጎች፣ በኮዶች ወይም መመሪያዎች አወጣጥ ሂደት ጥቅም ላይ ከሚውሉ የተሳትፎና የምክክር ዘዴዎች መካከል በጥቂቱ ፡- ➢ መረጃን ለህዝብ ተደራሽ ማድረግ፡- ማዕከላዊ የሆነ የበይነ መረብ መስመር ላይ የመረጃ ማስተላለፊያ መፍጠር፣ በመንግስት እና በመንግስት አካላት ድህረ ገፆች መረጃዎችን ማሳተም፣ ቴሌቪዠን፣ ሬዲዮ፣ ጋዜጣ እና በመሳሰሉ ሚድያዎች መረጃ ማሰራጨት እንዲሁም በሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች መረጃ ማስተላለፊያ፣ጋዜጣ እና ማህበራዊ ሚዲያ መረጃ ማስተላለፍ፣ ወዘተ ➢ ምክክር ማድረግ፡- የምክክር ጥሪዎችን በበይነ መረብ መስመር የመረጃ ማስተላለፊያዎች ወይም በመንግስት እና በመንግስት አካላት ድህረ-ገጾች፣እንደ ቴሌቪዥን እና ጋዜጣዎች ባሉ ሚድያዎች በመጥራት፣ በሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች መረጃ ማስተላለፊያዎች ወይም ጋዜጦች፣ በስብሰባዎች፣ በጠረዼዛ ዙሪያ በሚደረጉ ውይይቶች፣ በዜጎች አማካሪ ቡድኖች፣ በትኩረት ቡድኖች፣ በኢንተርኔት መስመር ላይ በሚደረጉ ውይይቶች ፣ በኢሜይል ዝርዝሮች፣በጽሁፍ አስተያየቶች፣ በባለሙያዎች የመወያያ መድረኮች፣ በህዝባዊ ክርክሮች ማውጣት፣ወዘተ ➢ ንቁ ተሳትፎ ማካሄድ፡- የተለያዩ ዘርፎችን ያካተቱ የስራ ቡደኖች፣ የባለሙያዎች ስብሰባዎች፣ የኢ-ሜይል ዝርዝሮች፣ የበይነ-መረብ መስመር ላይ የውይይት መድረኮች፣ ወዘተ ማድረግ ➢ ምክክር ላይ ማተኮር፡- የዜጎች ስብሰባዎች፤ምክክራዊ ምርጫዎች ወይም ጥናቶች፣ የዜጎች ተነሳሽነት ክለሳ፣ ያልታቀዱ ስልጠናዎች፣ ወዘተ ናቸዉ፡፡ Read More Download

በጽ/ቤቱ የተዘጋጀ ረቂቅ/ጊዜያዊ የአካታችነት ፖሊሲ

ይህ ፖሊሲ የህግና ፍትህ ጉዳዮች አማካሪ ጉባኤው የጉባኤውን የተለያዩና አካታች ዘላቂ የሆነ ውጤታማነትና ከፍተኛ የሆነ የአፈፃፀም ባህል እንዲዳብር ሁኔታዎችን ለመፍጠር ያለውን ዝግጁነቱን ያሳያል፡፡ ይህ የፖሊሲ ሰነድ ኢትዮጵያ በሴቶች ላይ የሚደርሱ መገለሎችን ለማስወገድ የወጣውን አለማቀፍ ኮንቬንሽን፣ የአፍሪካ ህብረት የስርአተ ፆታ ፖሊሲ እና የኢትዮጵያ ብሄራዊ የሴቶች ፖሊሲን በሚደግፍ መልኩ ተፈጻሚ ይሆናል፡፡ ፖሊሲው ተፈፃሚነቱ በአማካሪ ጉባኤው ሁሉም አመራሮች፣ ሰራተኞችና በጎ ፈቃደኞች እንዲሁም በቋሚነት፣ ለተወሰነ ጊዜ፣ በትርፍ ሰአት፣ በጊዜያዊነት የሚሰሩ የሚከፈላቸው እና የማይከፈላቸውን ሰራተኞች ላይ ተፈፃሚ ይሆናል፡፡ ሴክሬታሪያቱ የጉባኤውን አካታችነት ፖሊሲ መፈፀሙን የመከታተል፣ ውክልናና የአካታችነት ባህል በተቋምና በስራ አካባቢ ለመጨመር የሚያሥችሉ ዘደዎችን የማመቻቸት ሃላፊነት አለበት፡፡ Read More Download

TERM OF REFERENCE FOR MEMBER OF THE WORKING GROUPS ESTABLISHED BY THE LEGAL AND JUSTICE AFFAIRS ADVISORY COUNCIL

The FDRE Attorney General has established an Advisory Council composed of 13 legal professionals on June 29, 2018. This Council is expected to advise the government on the design and implementation of a comprehensive legal and justice sector reform. To discharge its mandate, the Advisory Council has already established several Working Groups composed of professionals with expertise on the thematic areas that fall within the purview of the Council. This document is supposed to serve as a guideline for members of Working Groups and facilitate their relationship with the Council. Read More Download

በሕግና ፍትህ ጉዳዮች ምክር ቤት የበጎ አድራጎት ድርጅቶችና ማህበራት ህግ ማዕቀፍ ማሻሻያ የቴክኒካል ባለሙያዎች ቡድን የውስጥ አሰራር ደንብ

የዚህ የአሰራር ደንብ አላማ ሰኔ 2010 ዓ.ም በመንግስት ውሳኔ የተቋቋመው የቴክኒካል ባለሙያዎች ቡድን የተሰጠውን ሀገራዊ ሀላፊነት በአግባቡ እንዲወጣ ለማስቻል የስራ ሂደቶቹን የሚመሩ ጥቅል መርሆችንና ዝርዝር የስብሰባና የውሳኔ አሰራሮችን መመስረት ይሆናል፡፡ Read More Download

HUMAN RIGHTS INFRASTRUCTURE WORKING GROUP TERMS OF REFERENCES

The Advisory Council has established Human Rights Infrastructure Working Group to undertake technical work and research necessary to identify laws and institution regarding human rights which need to be reformed. The terms of reference will introduce the composition and plan of action of the Human Rights Infrastructure Working Group. Read More Download

NON-DISCLOSURE POLICY (DRAFT)

This manual is intended to allow the LJAAC to establish a professional code of conduct regarding the disclosure of information by its staff and volunteers. Since the LJAAC’s advisory services to the government have the nature of legal advice, and given the lack of law that regulate this matter, the LJAAC set out this policy to ensure that its work is performed in a way that meets the ethical standards applicable to the services of legal advocates. Strict adherence to this policy will help the LJAAC to maintain professionalism and credibility in the justice system of the country. Read More Download