በሕግና ፍትህ ጉዳዮች ምክር ቤት የበጎ አድራጎት ድርጅቶችና ማህበራት ህግ ማዕቀፍ ማሻሻያ የቴክኒካል ባለሙያዎች ቡድን የውስጥ አሰራር ደንብ

በሕግና ፍትህ ፍትህ ጉዳዮች ምክር ቤት

የበጎ አድራጎት ድርጅቶችና ማህበራት ህግ ማእቀፍ ማሻሻያ የቴክኒካል ባለሙያዎች ቡድን የውስጥ አሰራር ደንብ

                                             

                                                 ክፍል አንድ

                                                    


                                                                ጠቅላላ1. አጭር ርዕስይህ የስነ-ስርአት ደንብየበጎ አድራጎት ድርጅቶችና ማህበራት ህግ ማእቀፍ ማሻሻያ የቴክኒካል ባለሙያዎች ቡድን የውስጥ አሰራር ደንብተብሎ ሊጠቀስ ይችላል።2. ትርጓሜየቃሉ አገባብ ሌላ ትርጉም የሚያሠጠው ካልሆነ በስተቀር በዚህ የስነ-ስርዓት ደንብ፡2.1. “ምክር ቤትማለት በአገር-አቀፍ ደረጃ የህግና ፍትህ ስርአት ማሻሻያ ስራዎችን ለማስተባበር፤ ለማሳለጥና በበላይነት ለመምራት በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ መንግስት ሰኔ 2010 . የተቋቋመ ነፃና ገለልተኛ አካል ነው፡፡2.2. “ፅህፈት ቤትማለት ምክር ቤቱን በመወከል የህግና ፍትህ ማሻሻያ ስራዎችን የእለት ተእለት ክንውን ለመከታተልና ለማስተባበር የተቋቋመ ተጠሪነቱም ለምክር ቤቱ የሆነ አካል ነው፡፡2.3. “የቴክኒካል ባለሙያዎች ቡድንማለት የበጎ አድራጎት ድርጅቶችና ማህበራት የህግ ማሻሻያ ስራዎችን፤ ተያያዥ ጥናቶችን፤ ምክረ-ሃሳቦችና ረቂቅ የህግ ሰነድ ማእቀፍ ለማደራጀት በምክር ቤቱ የተሰየመ ነፃ የባለሙያተኞች ስብስብ የሆነ አካል ነው፡፡3. አላማየዚህ የአሰራር ደንብ አላማ ሰኔ 2010 . በመንግስት ውሳኔ የተቋቋመው የቴክኒካል ባለሙያዎች ቡድን የተሰጠውን ሀገራዊ ሀላፊነት በአግባቡ እንዲወጣ ለማስቻል የስራ ሂደቶቹን የሚመሩ ጥቅል መርሆችንና ዝርዝር የስብሰባና የውሳኔ አሰራሮችን መመስረት ነው፡፡ክፍል ሁለትአጠቃላይ መርሆች4. የህገ-መንግስቱን መሰረታዊ እሳቤዎች ግንዛቤ ውስጥ ስለማስገባትየበጎ አድራጎት ድርጅቶችና ማህበራት የህግ ማእቀፍ ማሻሻያ ስራዎችን በማከናወንና ምክረ-ሃሳቦችን በማቅረብ ረገድ የቴክኒካል ባለሙያዎቹ ቡድን ዝርዝር ስራ ይዘት፡4.1. በኢ.... ህገ-መንግስት እውቅና ባገኙ መሰረታዊ መብቶችና ነፃነቶች፤4.2. ኢትዮጵያ በተቀበለቻቸው አለም-አቀፍና አህጉራዊ ስምምነቶች ላይ በተቀመጡ ተዛማጅ የሰብአዊና ዴሞክራሲያዊ መብት ማእቀፎች፤4.3. እንዲሁም የዜጎችን የመደራጀት መብት በማሳለጥ፤ የበጎ አድራጎት ተቋማትን ልዩ ሚና በመደገፍ እና የዲሞክራሲ ምህዳርን በማስፋት ረገድ በአለም-አቀፍ ደረጃ በተለዩ ምርጥ ተመክሮዎች ላይ ብቻ የተመሰረተና በዚሁ የሚመራ ይሆናል፡፡5. ሙያዊ ነፃነትና ገለልተኝነት5.1. የቴክኒካል ባለሙያዎች ቡድን አባላት ስራዎቻቸውን በነፃነት ያለማንም አካል፤ ተቋም ወይም ግለሰብ ጣልቃ-ገብነት ያከናውናሉ፡፡5.2. የቴክኒካል ባለሙያዎች ቡድን አባላት የተሰጣቸውን ሃላፊነት በፍፁም ገለልተኝነት ያከናውናሉ፡፡ ገለልተኝነትን ከሚፈታተነኑ ማናቸውም ሁኔታዎች የተጠበቁ መሆን አለባቸው፡፡5.3. የቴክኒካል ባለሙያዎች ቡድን አባላት ከዚህ የስራ ሃላፊነታቸው ጋር በተያያዘ በእጃቸው የሚገቡና በሙያዊ ሚስጥር ግዴታ (professional
secrecy/confidentiality)
የሚሸፈኑ ሰነዶችን፤ ውሳኔዎችንና መረጃዎችን ከፅ/ቤቱና ከምክር ቤቱ በስተቀር ለማናቸውም ሶስተኛ ወገን አሳልፈው አይሰጡም፡፡5.4. ማንኛውም አባል ሃሳቡን በነፃነት የመግለጽና የመደመጥ መብት ያለው ሲሆን በአንፃሩ የሌሎችን ሃሳብ የመግለጽ መብት ሊያከብር ይገበዋል፡፡6. የአባላት ግዴታዎች6.1. ለቡድኑ ዓላማና ተልዕኮዎች መሳካት የሚጠቅሙ ማናቸውንም ሥራዎች የመሥራት፤6.2. በቡድኑ ስብሰባ ላይ መገኘትና በንቃት መሣተፍ፤6.3. የሚሰጡትን ኃላፊነቶች በትጋት መወጣት6.4. የቡድኑን ሥራና ውጤታማነት ከሚጎዱ ተግባራት መቆጠብ፤6.5. የብዙኀኑን ውሣኔ የማክበርና የመተግበር፡፡ክፍል ሶስትየቴክኒካል ባለሙያዎች ቡድን አወቃቀርና የውስጥ አሰራር7. አወቃቀር7.1. የቴክኒካል ባለሙያዎች ቡድኑ እኩል ድምፅ ያላቸው ዘጠኝ አባላት ይኖሩታል፡፡7.2. የባለሙያዎች ቡድኑ የእለት መርሀ-ግብሮቹን የሚያስተዋውቅ እና አጠቃላይ የስራ ሂደቶችን የሚመራ አንድ ዋና አስተባባሪና አንድ ረዳት አስተባባሪ ይኖሩታል፡፡7.3. በየወቅቱ የሚካሄዱ ስብሰባዎች ቃለ-ጉባኤ አያያዝን በተመለከተ ዋና አስተባባሪው ጊዜያዊ (ad-hoc) ራፖርተር ሊሰይም ይችላል፡፡7.4. የባለሙያዎች ቡድኑ የተሰጠውን የስራ ሃላፊነት ሙሉ ለሙሉ እስኪያጠናቅቅ ድረስ ይቆያል፡፡8. ስለ መደበኛና -መደበኛ ስብሰባዎች8.1. የቴክኒካል ባለሙያዎች ቡድን መደበኛ ስብስባ ዘወትር ሐሙስ 930-1130 በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን የስብሰባ አዳራሽ ይካሄዳል፡፡8.2. የባለሙያዎች ቡድኑ አብዛኛው አባላት የተስማሙ እንደሆነ መደበኛ ስብሰባን በተለየ ቦታና ቀን ለማካሄድ፤ አሊያም የስራዎችን አጠቃላይ ፍሰት በመመልከት ተጨማሪ -መደበኛ ስብሰባ እንዲካሄድ ዋና አስተባባሪው አጀንዳ ማስያዝና ማስወሰን ይችላል፡፡8.3. ዋና አስተባባሪው በዚህ መልኩ የሚተላለፉ ውሳኔዎችን ሁሉም አባላት በቂ በሆነ ጊዜ ውስጥ እንዲያውቁት የማድረግ ሀላፊነት አለበት፡፡8.4. ዋና አስተባባሪው የቴክኒካል ባለሙያዎች ቡድኑን በመወከል የስራዎችን አካሄድና ወቅታዊ የስራ ሁኔታዎችን የሚመለከት ሳምንታዊ ሪፖርት ለምክር ቤቱ ፅህፈት ቤት ይልካል፡፡ ሪፖርቱ እንዳስፈላጊነቱ የተካሄዱ ክርክሮችን፤ ተአቅቦዎችንን፤ የተወሰኑ ውሳኔዎችንና የተደረሱ መደምደሚያዎችን በአጭሩ የሚተነትን ይሆናል፡፡9. ምልአተ-ጉባኤ9.1. በማናቸውም የስብሰባ ቀን ከባለሙያዎች ቡድኑ ጠቅላላ አባላት ቁጥር 51 ከዛ በላይ የተገኙ እንደሆነ ምልአተ-ጉባኤ የተሟላ ይሆናል፡፡9.2. ምልአተ-ጉባኤ መሟላቱን ለማረጋገጥ ዋና አስተባባሪው ወይም ረዳቱ የተገኙ አባላትን ስም ዝርዝርና ፊርማ የያዘ ሰነድ ያዘጋጃል፡፡10. የድምፅ አሰጣጥ ስነ-ስርአት10.1. ማናቸውም የውሳኔ ሃሳብ ምልአተ-ጉባኤ በተሟላበት የባለሙያዎች ቡድኑ ስብሰባ ላይ ከተገኙ አባላት 50% ድጋፍ ያገኘ እንደሆነ የፀና ይሆናል፡፡10.2. እያንዳንዱ አባል አንድ ድምፅ ብቻ ይኖረዋል፡፡ በስብሰባ ላይ ያልተገኘ አባልን በመወከል ድምፅ መስጠት አይፈቀድም፡፡10.3. ውሳኔዎች በዲሞክራሲያዊ ማዕከላዊነት የሚተላለፉ ሲሆን ሃሳቡ ተቀባይነት ያላገኝ ማንኘውም አባል የልዩነት ሀሳቡ ከአብላጫው ውሳኔ ጋር እንዲካተትለት ጽፎ ማቅረብ ይችላል፡፡10.4. የድጋፍ፤ የመንፈግ ወይም የተአቅቦ ድምፅ ፈቃድ የሚሰጠው እጅ በማውጣት ነው፡፡ ይህም የአስተባባሪውን አሊያም የረዳቱን ጥሪ ተከትሎ የሚፈፀም ይሆናል፡፡10.5. ውሳኔ ያረፈበት እያንዳንዱ ረቂቅ ቃለ-ጉባኤ በቀጣይ የስብሰባ ቀን በአጀንዳነት ቀርቦ ይፀድቃል፡፡ በውሳኔው ቀን በተገኙ አባላት ሁሉ መፈረም ይኖርበታል፡፡10.6. የጉባኤውን ውሳኔ ተከትሎ ቀጣይ ስራን የሚጠይቁ ጉዳዮች የተለዩ እንደሆነ በዚህ ረገድ ሀላፊነት የተሠጣቸው አባላትን ስም ዝርዝርና የስራ ድርሻ ያካተተ የኤሌክትሮኒክ መልእክት ዋና አስተባባሪው በሁለት ቀናት ውስጥ ለሁሉም አባላት ይልካል፡፡11. የአሰራር ደንቡን ስለማሻሻል11.1. ማናቸውም የቴክኒካል ባለሙያዎች ቡድኑ አባል ይህ የአሰራር ደንብ እንዲሻሻል አጀንዳ እንዲያዝ ጥያቄ ማቅረብ ይችላል፡፡11.2. ሆኖም የዚህ አይነት ጥያቄ ከጠቅላላው አባላት ቢያንስ 2/3 ድምፅ መፅደቅ ይኖርበታል፡፡12. የአሰራር ደንቡ የሚጸናበት ጊዜይህ የውስጥ አሰራር ደንብ ከዛሬ ሐምሌ 5 ቀን 2010 . ጀምሮ የቴክኒካል ባለሙያዎች ቡድኑ ስራውን ሙሉ ለሙሉ እስኪያጠናቀቅ ድረስ ተፈጻሚ ይሆናል። ሐምሌ 5 ቀን 2010 .አዲስ አበባ

0 Comments

Leave a Comment