የሁለተኛ ዓመት የሥራ ዕቅድ


1.    መግቢያ

 

የሕግ እና የፍትሕ ጉዳዮች አማካሪ ጉባዔ የሁለተኛ ዓመት የሥራ ዘመን ዕቅድ ሦስት ዋና ዋና ዘርፎችን የሚይዝ ይሆናል፡፡ አንደኛው መጀመሪያው ዓመት የሥራ ዕቅድ ተይዘው የነበሩ እና በተለያየ ምክንያት መጠናቀቅ ያልቻሉ ስራዎችን ማጠናቀቅ ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ በአገሪቷ የተጀመሩ የፍትህ ማሻሻያ ስራዎችን ውጤታማነት እና ዘላቂነት ለማረጋገጥ ወይም ለመደገፍ የሚያስችሉ ስልቶችን መዘርጋት ነው፡፡ በመጨረሻም በአማካሪ ጉባዔው የሥራ ወሰን ስር ሊወድቁ የሚችሉ አዲስ ስራዎችን መስራት ይሆናል፡፡ አማካሪ ጉባዔው በሁለተኛው ዓመት የሥራ ዘመኑ ያጋጠሙ ችግሮችን እና የቀደሙ ልምዶችን ታሳቢ በማድረግ በፍትሕ ማሻሻያ ስራዎች ላይ የሚያጋጥሙ ተግዳሮቶችን ለመፍታት ጠንካራ እንቅስቃሴ የሚያደርግ ይሆናል፡፡ ይህም ከአለፈው ዓመት የተሸጋገረ የአማካሪ ጉባዔው ቁልፍ ተግባር እንደሚሆን ይጠበቃል፡፡

2.   የመጀመሪያው ዓመት ስራዎችን ማጠናቀቅ

 

አንዳንዶቹ በመጀመሪያው የሥራ ዘመን በዕቅድ የተያዙ ስራዎች በተለያዩ ተገማች እና ድንገተኛ በሆኑ ምክንያቶች ወደ ሁለተኛዉ የሥራ ዘመን ሊሸጋገሩ እንደሚችሉ ይጠበቃል፡፡ ከነዚህ ስራዎች መካከል በጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ፣ በሚንስትሮች ምክር ቤት ወይም በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሕግ ማውጣት ስራዎች ሂደት ላይ ድጋፍ ከማድረግ ጋር የተያያዙ ተግባራትን ማጠናቀቅን በምሳሌነት መጥቀስ ይቻላል፡፡ አማካሪ ጉባዔዉ ከላይ በተጠሱት ተግባራት ላይ ሙሉ ቁጥጥር የሌለዉ መሆኑን ተከትሎ ዕንደሁኔታዉ በሚከተሉት ተግባራት ላይ ትኩረቱን አድርጎ ይሰራል፡-

·        
የንግድ ሕጉን መጻፍ 3 እና 4 (ስለኢንሹራንስ ፣ስለውርርዶች ፣ስለኪሳራ ጨዋታ ፣ስለሚተላለፉ የገንዘብ ሰነዶችና ስለባንክ ስራዎችየመጀመሪያ ደረጃ የማርቀቅ ስራ፡፡ምንም እንኳን እነዚህ

·        
ተግባራት በመጀመሪያው የሥራ ዘመን እንዲጠናቀቁ የታቀደ ቢሆንም በስራ ቡድኑ እና በአማካሪ ጉባዔው ስራው ለሁለት ተከፍሎ እንዲሰራ በመታመኑ በነዚህ መጻፍት ላይ የታቀደው ስራ ወደ  ሁለተኛ ዓመት እንዲተላለፍ ሆኗል፣ 

·        
በወንጀል ፍትሕ አስተዳደር የሥራ ቡድን ተጀምሮ የነበረው እና በሌሎች ስራዎች ምክንያት ወደኃላ የቀረውን የኢትዮጲያ የወንጀል ፍትሕ ሥርዓት ግምገማ ማጠናቀቂያ በሁለተኛ የሥራ ዘመን የሚቀጥል ይሆናል፣

·        
የሕግ እና ፍትሕ አማካሪ ጉባዔ የሚያከናውናቸው እንደ ሪፖርት፣ ሀተታ ዘምክንያት፣ የሕግ  ማብራሪያ፣ የሕግ ማውጣት ሂደት ስራዋችን እና ሌሎች ተጨማሪ ማስረጃዎችን ከስራ ጎን ለጎን  በማደራጀት በመጨረሻም ለህትመት የሚሆኑትን ስራዎች በማሳተም እንዲጠናቀቅ ማድረግ፡፡

 

3.   የአፈጻጻም ድጋፍ ክትትልና እና ምዘና

 

የአማካሪ ጉባዔው የመጀመሪያው ዓመት የሥራ ዘመን እየተጠናቀቀ መሆኑን ተከትሎ አማካሪ ጉባዔዉ ትኩረቱን ለሰብዓዊ መብት፣ ዴሞክራሲ እና የሕግ የበላይነት መረጋገጥ አይነተኛ ሚና የሚያበረክቱ የማሻሻያ ፓኬጆች አፈጻጸም ወደ መደገፍና መመዘን ስራ የሚያዞር ይሆናል፡፡ ይህ የሆነበት ምክንያትም በአግባቡ የተቀረጹ ሕግጋት መኖር ብቻውን የለውጥ ስራውን ዋና ግብ ለማረጋገጥ በቂ አይሆንም ከሚል እሳቤ ነው፡፡ በመሆኑም የሕግና ፍትሕ ጉዳዮች አማካሪ ጉባዔ የአዳዲስ ሕጎችን ተግባራዊነት ለመደገፍ ቀደምት ፣ወቅታዊና ተነፃፃሪ ልምዶችን በመጠቀም የአፈጻጻም ሂደቱን ይደግፋል፤ እንዲሁም የኢትዮጲያ መንግስት የለውጡን ውጤታማነት ለመለካት የሚችልባቸውን አመልካቾች (መለኪያዎችንያካተተ ሥርዓት ቀርጾ ያቀርባል፡፡ ይህ ተግባር በሲቪል ማህበረሰቡ፣ በመገናኛ ብዙሃን ሕግ፣ በፀረ-ሽብር አዋጁ፣ በዴሞክራሲ ተቋማት፣ በአስተዳደር ሕጉ፣ በወንጀል ሥነ-ሥርዓት እና የሕግ ስራዎችን የሚሰሩ የሥራ ቡድኖች ያዘጋጇቸውን ሕጎች አፈጻጸም መገምገምን የሚያካትት ይሆናል፡፡

 በዚህ ምድብ ውስጥ ያለው ሥራ የሚያካትተው አማካሪ ጉባዔዉ የሰጣቸዉ የየመፍትሔ ሀሳቦች ምን ያህል ተቀባይነት እንዳገኙ አናበስራ ላይ ሲውሉም ያላቸው ተፅህኖ በመከታተልና በመገምገምባጠቃላይ ስራውን መመዘን ሲሆን፣ እንዲሁም የማሻሻያ ሂደቱ ግቡን እንዲመታ መንገድ ማሳየት እና ለአስፈጻሚው አካል ተቋማዊ ድጋፍ ማድረግን ያካትታል፡፡
አማካሪ
ጉባዔው የሚደረጉ ማሻሻያዋችና የሚወጡ ህጎችን የመተግበር የመጀመሪያ ኃላፊነት በየዘርፉ አስተዳዳሪዋች ላይ የሚወድቅ መሆኑን በማስመር ለነዚህ ተቋማት ድጋፍና ክትትል የሚያደርግ ይሆናል፡፡

እነዚህ ተቋማት የመሪነቱን ሚና እንዲወስዱ ማድረጉ ህጉ የሚጠይቀዉ ከመሆኑም ባሻገር ይህ አይነቱ አደረጃጀት የየዘርፉ ተቋማት በረዥም ጊዜ ሂደት ለዉጡን በዘላቂነት ለመምራት የሚያስችላቸዉን አቅም ለማዳበር የሚያግዛቸዉ ይሆናል፡፡ነገር ግን የሕግና ፍትሕ ጉዳዮች አማካሪ ጉባዔ በህግ ማሻሻል ሂደቱ  ከፍተኛ የአማካሪነት ሚና እንደተጫወተ አካል የማሻሻያዋቹን ተፈፃሚነት የመከታተልና የመመዘን እንዲሁም አስፈላጊዉን ድጋፍ የማድረግ ስልጣን የሚኖረዉ ይሆናል፡፡በተጨማሪም በቀደሙ ተቋማዊ  አሰራሮች ከተተበተቡ እና የተሻሩ ሕገ-ደንቦችን በሚተገብር የሰዉ ሀይል ከተሞሉት የየዘርፉ አስፈጻሚዎች  በተቃራኒ አማካሪ ጉባዔዉ የሕግ ማሻሻያዉ በተቋማቱ አፈጻጸም እና ስራ ላይ የሚኖረዉን የላቀ አስተዋጾ ለማረጋገጥ ከፍተኛ ሚና ይጫወታል፡፡

 

4.    አዲስ እና ዋና ዋና የሁለተኛ ዓመት ተግባራት

 

ከአንደኛው ዓመት ከተሸገሩ ስራዎች በተጨማሪ የሕግና ፍትሕ ጉዳዮች አማካሪ ጉባዔ በሁለተኛው ዓመት የሥራ ዘመን ተጨማሪ አዳዲ ስራዋችን በመጀመሪያዉ አመት ከተቋቋሙየሥራ ቡድኖች ጋር የተያያዙ ወይም በአዲስ መልክ የሚያዙ ስራዎች ይኖራሉ፡፡ በቀጣይ የሚሰሩ ስራዎች እና የሥራ ቡድኖች በአማካሪ ጉባዬ ከሚጸድቁ በኃላ አማካሪ ጉባዔዉ በሚያወጣዉና በጽ/ቤቱ በሚተገበር የጊዜ መርሀ ግብር መሰረት የሚከናወኑ ይሆናሉ፡፡

 

4.1   የፍትሕ ማሻሻያ ንዑስ ፕሮግራም

 

ከመጀመሪያው የሥራ ዘመን ከቀጠሉ ተግባራት በተጨማሪ የሚከተሉት የሥራ ቡድኖች በዚህ ንዑስ ፕሮግራም ስር ተዋቅረዋል፡-

 

•     የመሰብሰብ እና ተቃውሞ የማድረግ ነፃነት የሥራ ቡድን፣

 

•     የመዘዋወር ነፃነት የሥራ ቡድን፣

 

•     የሰብዓዊ መብት ሕጎችና ተቋማት መዋቅር የሥራ ቡድን፣ እና

 

•     ዘላቂ የሕግና ፍትሕ ሥርዓት ማሻሻያ የሥራ ቡድን።

 

 

 4.2  የወንጀል ፍትሕ ሥርዓት ንዑስ ፕሮግራም

 

የሕግና ፍትሕ ጉዳዮች አማካሪ ጉባዔ የወንጀል ሥነ ስርዓት ሕጉን ለጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ካስረከበ በኃላ የወንጀል ሥነ ስርዓት የሥራ ቡድን ትኩረቱን ወደ ወንጀል ፍትሕ ስርዓት ግምገማ በመመለስ በኢትዮጲያ ያለውን ነባራዊ ሁኔታ የማጥናት ስራውን የሚያጠናቅቅ ይሆናል፡፡ተግባረዊ (empirical) እና አይነታዊ (qualitative) የሆነው የጥናቱ ውጤት ቀጣይ የሥራ ቡድን አካሔድ እና የሥራ ቅደም ተከተልን የሚወስን ይሆናል፡፡

 

4.3  የፍትሐ ብሔር እና የንግድ ሕግ ንዑስ ፕሮግራም

በዚህ ንዑስ ፕሮግራም በመጀመሪያ በአንድ የሥራ ቡድን ስር ተቋቁሞ የነበረዉ የፍትሐ ብሔር እና የንግድ ሕግ የሥራ ቡድን በሁለት ቡድኖች ተከፍል፡፡የንግድ ሕግ የሥራ ቡድን የንግድ ሕጉ መጻሐፍ 3 እና 4 የማጠናቀቅ ስራን የሚሰራ ይሆናል፡፡የፍትሐ ብሔር ሕግ የሥራ ቡድን ደግሞ በወቅቱ ያሉ ለሕጉ መሻሻል ገፊ የሚሆኑ ምክንያቶችን ከሕጉ እና ከሕጉ አፈጻጻም አንጻር ያሉት ችግሮች የሚለይ ይሆናል፡፡በፍትሐ ብሔር እና በንግድ ሕግ የሥራ ቡድን በሁለተኛው የሥራ ዘመን የሚከተሉትን ስራዎች በእቅድነት ተይዘዋል፡-

   •     የንግድ ሕግ የሥራ ቡድን፣

 

•     የሲቪል ምዝገባ ሥርዓት ማሻሻያ የሥራ ቡድን፣

 

•     የሕጎች ግጭት (conflict of laws ወይም private international law) የሥራ ቡድን፡፡

  

 4.4. የዴሞክራሳዊ ተቋማት ንዑስ ፕሮግራም

አሁን በስራ ላይ ያለዉ በህግና ፍትህ ጉዳዮች አማካሪ ጉባዔና በኢትዮጲያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ መካከል ያለዉ አደረጃጀት ከጠቅላይ /ህግ ጋር በመተባበር ከኢትዮጲያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን፣ከዕንባ ጠባቂ ተቋም፣ ከፌደሬሽን ምክር ቤት እና ከሕገ-መንግስት አጣሪ ጉባዬ ጋር በንዑስ ፕሮግራሙ አፈፃፀም ዙሪያ ዉይይት ማድረግ የጀመረ ሲሆን አማካሪ ጉባዔዉ የሰባዊ መብቶች ኮሚሽን የሥራ ቡድን፣የህዝብ እምባ ጠባቂ ተቋም የሥራ ቡድንና እንዲሁም ከሚመለከታቸዉ አካላት ጋር ከተነጋገረ በኋለ የህገ መንግስት ጥናት ቡድን የሚያቋቁም ይሆናል፡፡ 

 4.5  የሕግ እና ተዛማጅ አገልግሎቶች ንዑስ ፕሮግራም

 የሕግ እና ተዛመጅ አገልግሎቶች የስረ ቡድን የሕግ ማርቀቅ ስራውን ካጠናቀቀ በኃላ ትኩረቱን ወደ ሕግ ነክ ሙያዎች አገልግሎት በማዞር የሕግ ባሙያዎችን፣ሽምግልና ፣የአደራ አስተዳደር ፣ምርመራ እና ተመሳሳይ አገልግሎት ላይ ይሰራል፡፡በተጨማሪም የሥራ ቡድኑ በታሰበዉ የህግ ስራ ቁጥጥር ማዕቀፍ የአማካሪ ጉባዔዉ የትግበራ ድጋፍ ምን ሊሆን እንደሚችል በተጠየቀ ጊዜ ማብራሪያ ይሰጣል፡፡ 

4.6   የሕግ ማውጣት ሂደት እና የአስተዳደ ሕግ ንዑስ ፕሮግራም

 

የአስተዳደር ሕግ እና የሕግ ማውጣት የሥራ ቡድን የአስተዳደር ሕግ ላይ ያለውን ስራ ካጠናቀቀ በኋላ ወደ ሕግ ማውጣት ሂደት ስራው ይገባል፡፡ አካሄዱም አማካሪ ጉባዔው ከዚህ ቀደም ስራዎችን በሚጀምርበት አግባብ የመነሻ ወይም የዳሰሳ ጥናት በማካሄድ የሕግ ማውጣቱ ሂደቱን ምን መምሰል እንዳለበት የሚያረጋግጥ እና የሚመራ ይሆናል፡፡

 

 4.7  የሕግ ሥልጠና እና ትምህርት ንዑስ ፕሮግራም

 

በሕግ ትምህርት ውስጥ ማሻሻያው የሚኖረው ተጽዕኖ የሚከታተል እና በተጨማሪም በሕግ ትምህርት ሥርዓት ላይ ማሻሻያ ለማድረግ የሚረዳ አንድ የሥራ ቡድን በሁለተኛው ዓመት ይቋቋማል፡፡

 

5.   የሕግና ፍትሕ ጉዳዮች አማካሪ ጉባዔ፣ ፀሐፊ እና የሥራ ቡድኖች መዋቅር

 

የሕግና ፍትሕ ጉዳዮች አማካሪ ጉባዔ የወቅቱ አወቃቀር በቻርት (ኦርጋኖግራምከታች ቀርቧል፡፡ 

 

 

 

 

  

 

 

0 Comments

Leave a Comment