የአንደኛ ዓመት የስራ ክንውን ሪፖርት

                                                                               የአንደኛ ዓመት የስራ ክንዉን ሪፖርት

1.መግቢያ

የኢ... ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ሀገራችን ያለችበትን የለውጥ ሂደት ውጤታማነት ለማረጋገጥ የተለያዩ የተቋማትና የሕግ ማሻሻያ ስራዎችን እየሠራ እንደሚገኝ ይታወቃል፡፡ የነዚህ ማሻሻያ ስራዎች ዓላማ ለውጡ ተቋዋማዊ፣ ሁሉን አቀፍና በጥናት በተደገፈ አካሄድ ተግባራዊ ተደርጐ የሕግ በላይነትና ፍትህ የሠፈነባት፣ ሰብዓዊ መብቶች የተከበሩባት፣ በዲሞክራሲያዊ አግባብ የምትመራ ሀገር መገንባት ነው፡፡ ይህን ዓላማ ለማሳካት የኢ... ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ከፍተኛ ልምድና ብቃት ያላቸውን አስራ ሶስት የሕግ ባለሞያዎች ያቀፈ የሕግና ፍትህ ጉዳዮች አማሪ ጉባዔ አቋቁሟል፡፡ አማካሪ ጉባዔዉ የሰብዓዊና ዴሞክራሲ መብቶችን እንዲሁም የሕግ የበላይነትን የመሳሰሉ ሕገ-መንግስታዊ መርሆዋች መሰረት በማድረግ ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግን በሕግና ፍትሕ ማሻሻያ ጉዳዮች ላይ የማማከር ስልጣን የተሰጠዉ ሲሆን የአማካሪ ጉባዔዉ ስልጣንና ተግባራት በዋናነት የሚከተሉትን ያጠቃልላል፡-

  በዴሞክራሲያዊ አስተዳደር ተቋማት ዉጤታማነት ላይ ተፅዕኖ ባላቸዉ ሕጎች፣ ተቋማትና አሰራሮች ላይ ጥልቅ የሆነ ጥናትና ግምገማ ማድረግ፤

 ተጠያቂነት የሰፈነበት የመንግስት አስተዳደር ለማስፈን፣ የሕግ የበላይነትን ለማረጋገጥና -ገመንግስታዊ መብቶችን ሙሉ በሙሉ ለማረጋገጥ በሚደረገዉ ጥረት ያጋጠሙ ተግዳሮቶችን መለየት፣ ማጥናትና መሰብሰብ፤

   ሕጋዊና ተቋማዊ ችግሮችን ሊፈቱ የሚችሉ አይነታዊ(ገላጭ) የጥናት ውጤቶች ላይ መሠረት ያደረጉ የማሻሻያ ሀሳቦችን የተጠኑና በፕሮግራም የተደገፉ እዉነታ ላይ የተመሰረቱ የማሻሻያ ፓኬጆችን ለጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ማቅረብ፡፡

አማካሪ ጉባዔዉ ስልጣንና ተግባሩን በሚገባ መወጣት ይችል ዘንድ የለት ከዕለት የአስተዳደር ስራ የሚያከናዉን የአማካሪ ጉባዔ ፅህፈት ቤት፣ በጎ ፈቃደኞችን እና ቋሚ ባለሙያዋችን ያካተተ የስራ ቡድኖች አቋቁሟል፡፡ የጉባዔዉ /ቤት አስተዳደራዊና የቴክኒክ ድጋፎችን ለስራ ቡድኖችና ለጉባዔዉ የሚሰጥ ሲሆን እያንዳንዱ የስራ ቡድን በተለያዩ ሕጎች ላይ ጥልቅ ጥናት በማድረግ የማሻሻያ ሀሳቦችን ያቀርባል፡፡ ይህ ዓመታዊ ሪፖርት በፕሮግራሙ አንደኛ ዓመት ዉስጥ በአማካሪ ጉባኤዉና በስሩ ባሉት የጉባኤዉ /ቤት እና የስራ ቡድኖች የተከናወኑ ስራዋችንና ያጋጠሙ ተግዳሮቶችን በማካተት እንደሚከተለዉ ቀርቧል፡፡

 1.1  የለውጥ ሂደቱ ዳራ

 አሁን በኢትዮጵያ እየተካሄደ የሚገኘዉ የሕግና ፍትሕ ማሻሻያ ፕሮግራም 20ኛዉ ክፍለ ዘመን መጀመሪያ ጀምሮ ሲካሄድ የቆየዉን የሕግና ፍትሕ ማሻሻያ ተከትሎ የመጣ ነዉ፡፡ በዚያ ዘመን ኢትዮጵያ ሕገ-መንግስታዊና ባህላዊ የሕግ ስርቷን ለማሻሻል ወደ ተለያዩ የዉጭ ሀገር የሕግ ሞዴሎች ማማተር ከመጀመሯም በተጨማሪ ዘመናዊነትንና የኢኮኖሚ ዕድገትን እዉን ለማድረግ በማሰብ ከፍተኛ የሆነ የሕግ ለዉጥ እንቅስቃሴዋች ዉስጥ ገብታለች፡፡ በኮሚኒስታዊ ርዕዮት ዓለም የታገዘው የደርግ መንግስት ወደ ስልጣን መምጣቱን ተከትሎ በኢትዮጵያ የነበረዉ የሕግና ፍትሕ ማሻሻል ሂደት ለጊዜዉ ተዳክሞ የቆየ ቢሆንም ከደርግ መንግስት ዉድቀት በኋላ በተለይም ደግሞ የኢፌዴሪ ሕገ-መንግስት መፅደቁን ተከትሎ ከፍተኛ የሕግ ማሻሻያዋች ተደርጓል፡፡

ይሁን እንጂ ቀድሞ ሲደረጉ የነበሩት የሕግና ፍትሕ ሥርዓት የማሻሻል ጥረቶች በአጠቃላይ በቴክኒክ ረገድ ጥሩ የሚባሉ ቢሆኑም በየጊዜዉ በነበሩ አፋኝ የመንግስታት ፖሊሲዎች ምክንያት የታለመላቸዉን አላማ ሳያሳኩ ቀርተዋል፡፡ ይሁን እንጅ ጠቅላይ ሚኒስቴር / አብይ አህመድ በሚያዝያ 2010. ወደ ስልጣን ከመጡ በኋላ መንግስታቸዉ በቀደመዉ ጊዜ ለተፈፀሙ የሰብዓዊና ዴሞክራሲያዊ የመብት ጥሰቶች ይቅርታ በመጠየቅ፣በሺዎች የሚቆጠሩ እስረኞችን በይቅርታና ምህረት በመልቀቅ፣ በመገናኛ ብዙሃንና በበይነመረብ ላይ የነበሩ ገደቦችን በማንሳት፣በሽብርተኝነት የተፈረጁ የፖለቲካ ድርጅቶችን ከሽብርተኝነት መዝገብ በማዉጣት እንዲሁም በስደት የነበሩ ጋዜጠኞች፣የማህበረሰብ አንቂዋችና የመገናኛ ብዙሃን ተቋማት ወደ ሀገራቸዉ እንዲገቡ በመፍቀድ አፋጣኝ የአጭር ጊዜ የመፍትሄ እርምጃችን ወስደዋል፡፡ መንግስት እንደ መካከለኛ ጊዜ ዕቅድ አፋኝና ለሰብዓዊ፣ ዴሞክራሲያዊ እና ሕገ-መንግስታዊ መብቶች መከበር እንቅፋት የሆኑ እንደ ፀረ ሽብር፣የመገናኛ ብዙሃንእና የሲቪል ማህበረሰብ ሕጎችን ጨምሮ ለማሻሻል ቃል መግባቱ ይታወሳል፡፡

 ለዴሞክራሲያዊነትና ሰብዓዊ መብቶች መከበር ትኩረት ከሰጠዉ አዲስ ፖለቲካዊ ነፃነት ጋር ተያይዞ አሁን እየተካሄደ የሚገኘዉ የሕግና ፍትሕ ሥርዓት ማሻሻል ሂደት ትኩረቱን በእነዚህ አዳዲስ የትኩረት አቅጣጫዋች ላይ አድርጓል፡፡ በተመሣሣይ መንግስት ይህ የሕግና ፍትሕ ማሻሻያ ሂደት የተለያዩ የሕግ ባለሞያዎችንና የሚመለከታቸዉን አካላት በማሳተፍ ነፃና ተቋማዊ በሆነ መልኩ እንዲከናወን ወስኗል፡፡

 ከላይ የተጠቀሱትን የመንግስት የትኩረት አቅጣጫዎች እውን ለማድረግ በማሰብ የማሻሻያ ሂደቱን በነፃነት የሚመራ የሕግና ፍትሕ ጉዳዮች አማካሪ ጉባዔ ተቋቁሟል፡፡ አማካሪ ጉባዔዉ ከፖለቲካዊ ፍላጎት ይልቅ ነፃነትን፣ሙያን፣ስነ-ምግባርንና የአባላቱን አእዕምሮ መሠረት በማድረግ በማሻሻያ ሂደቱ ዉስጥ የመሪነት ሚና ይጫወታል፡፡ አማካሪ ጉባዔዉ የተቋቋመበትና የተዋቀረበት መንገድ በማሻሻያ ሂደቱ በኢትዮጵያና በዉጭ ሀገር የሚገኝን ልምድና እዉቀት በመጠቀም በስምንት የትኩረት አቅጣጫዋች ላይ መንግስትን ለማማከር ያለመ ነዉ፡፡

 1.2. ዓላማ

የሕግና ፍትሕ ጉዳዮች አማካሪ ጉባዔ ዋና ዓላማ የኢትዮጵያ መንግስት ፍትሕን ለማሻሻል፣ የሕግ የበላይነትን ለማስከበር፣ ሰብዓዊ መብቶችን ለመጠበቅና እዉነተኛ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሀገር ለመገንባት የሚያደርገዉን ጥረት ዉጤታማ በሆነ መልኩ ማማከር ነዉ፡፡

 2. የትግበራ አደረጃጀትና የሰዉ ሀይል 

አማካሪ  ጉባዔዉ በመመሪያ ቁጥር 24/2010(አባሪ 2) መሠረት የተመሰረተ ሲሆን በኢትዮጵያ እየተካሄደ የሚገኘዉ የሕግና ፍትሕ ማሻሻል ሂደት አጠቃላይ አቅጣጫ ምን መሆን እንዳለበት መንግስትን የማማከር ኃላፊነት የተጣለበት ተቋም ነዉ፡፡ የአማካሪ ጉባዔዉ ዉሳኔዎችና የዉሳኔ ሀሳቦች አስገዳጅነት ባይኖራቸዉም እንኳን ጉባዔዉ የሚሰጣቸዉ የፖሊሲ አቅጣጫዎች ትልቅ ቦታ የሚሰጣቸውና በአጠቃላይ ተቀባይነት የሚያገኙ ናቸዉ፡፡ የአማካሪ ጉባኤዉና የጉባኤዉ ፅ/ቤት እንዲሁም ሌሎችበስሩ የተቋቋሙ ተቋማት አወቃቀር፣ ተግባር፣ ስልጣን እና ኃላፊነት በማቋቋሚያ መመሪያዉና(አባሪ 2) በአባሪ በተቀመጡት ደንብና

 ሥርዓት መሠረት ተዘርዝሮ ይገኛል፡፡ አሁን እየሰሩ የሚገኙና የቀድሞ የጉባኤዉ አባላት አጭር የህይወት ታሪክ ከዚህ ሪፖርት ጋር በአባሪ አንድ ተያይዟል፡፡ የሕግና ፍትሕ ጉዳዮች አማካሪ ጉባዔ ተቋማዊ አወቃቀር ከዚህ በታች በሚታየዉ ስዕላዊ ቀርቧል፡-

  

3. 1 ዓመት የስራ ዝርዝርና መርሀ-ግብር

 የሕግና ፍትሕ ጉዳዮች አማካሪ ጉባዔዉ በመጀመሪያው የስራ ዘመን የስራ ትግበራ መዋቅር መዘርጋት፣ መዋቅሩን በተወዳዳሪ ሰራተኞች ማደራጀት፣ ፍኖተ ካርታ ማዘጋጀት፣ የስራ ቡድኖችን ማዋቀር፣ የጽ/ቤቱን እነዲሁም የጉባዔዉን ስራ የማስጀመር ተግባራት ላይ ትኩረት ሰጥቶ ሰርቷል፡፡ በጉባዔዉ እና በጽ/ቤትና ተነሳሽነት የሚከተሉትን ተግባራት ተከናዉኗል፡

 - የስራ ቡድኖችንና የጽ/ቤቱን አባላት የመለመለ ሲሆን በቀጣይም እንዳስፈላጊነቱ ተመሳሳይ ስራ ያከናዉናል፣

  - የጥናት ቡድኖችን የስራ አጀማመር ሪፖርት ተቀብሎ ገምግሟል፤፣   

-  ድረ-ገፅ፣ ኢሚል እና ድራይቭ አካዉንቶች ከፍቷል፣ 

 - ለአማካሪ ጉባዔዉ የቀጥታ ድምፅ መስጫ ስዐርት ዘርግቷል፣, የስራ ቡድኖች የሥነ-ምግባር ደንብ በማዘጋጀት አፅድቋል፣ 

 -  አማካሪ ጉባዔው የሚመራበትን ውስጠ ደንብ አፅድቆ ተግባራዊ አድርጓል፣  

 - በተጨማሪም ጉባዔው የማሻሻያ ሥራውን የሚመራበት፣ አጠቃላይ ዓላማውንና የትኩረት አቅጣጫውን የሚያሳይ ፍኖተ ካርታ አዘጋጅቶ አፅድቋል፣ 

 -  የህዝብ ተሳትፎ ስትራቴጂ ስነድ ተዘጋጅቶ በስራ ላይ ውሏል፣  

 -  የጉባዔዉ /ቤት የብዝሃነትና አካታችነት ፖሊሲ አዘጋጅቷል፣  

-  የጉባዔዉ /ቤት ሚስጥር ጠባቂነትና መረጃ ያለማዉጣት ፖሊሲ አዘጋጅቷል፣  

-  የገንዘብ ድጋፍና ወይም ሌሎች ትብብሮችን ዓለማቀፍ ተቋማት አግኝቷል፣ 

-  አስፈላጊ በሆነ ጊዜ በገንዘብ ድጋፍና በአጋር ድርጅቶች ትብብር በመታገዝ በየዘርፉ የሀገር ዉስጥና ዓለም አቀፍ ባለሙያዋችን ቀጥሯል፡፡

 

  የስራ ቡድኖች መቋቋማቸዉን ተከትሎ የአማካሪ ጉባዔዉ አቅም በከፍተኛ ሁኔታ ጨምሯል፡፡ ይኸዉም 143(አንድ መቶ አርባ ሦስት) የረጅም ጊዜ በጎ ፈቃደኞች፣ 8(ስምንት) የሙሉ ጊዜ ተቀጣሪዎች፣ 13(አስራ ሦሥት) የሀገር ዉስጥና የዉጭ የአጭር ጊዜ አማካሪዎች በአማካሪ ጉባዔዉ ስር እየሰሩ ይገኛሉ፡፡ ተቋሙን በሰዉ ኃይል የማደራጀት ስራዉ እንደቀጠለ ሲሆን አማካሪ ጉባዔዉ በመጀመሪያ ዓመት የስራ ዘመኑ(በኢትዮጵያ አቆጣጠር 2011 /) ያለጉባዔዉ ተሳትፎ የማይታሰቡ ሕጋዊና ተቋማዊ ለዉጦችን ለማሳካት ተቃርቧል፡፡ በዕቅዱ መሠረት አማካሪ ጉባዔዉ ከሕግ ማውጣት ሂደት፣ ከፍትሕ ሥርዓት፣ ከወንጀል ፍትሕ ሥርዓት፣ ከፍትሐብሔርና አስተዳደር ሕግ ፍትሕ ሥርዓት እና ከዴሞክራሲያዊ ተቋማት ንዑስ መርሀ-ግብሮች ላይ የመጀመሪያ ደረጃ ሕጎችን የማውጣትና ተቋማዊ ለውጥ ላይ ትኩረቱን አድርጎ ሰርቷል፡፡ በመጀመሪያዉ ዓመት መርሀ ግብር አማካሪ ጉባዔዉ ያከናወናቸዉ ዋና ዋና ተግባራት እንደሚከተለዉ ይቀርባል፡፡

 3.1 የፍትሕ ጉዳዮች የስራ ቡድን

በአማካሪ ጉባዔው የተቋቋመው የዳኝነት ጉዳዮች የጥናት ቡድን ስራውን የዳኝነት አካላት ነፃነትን በተመለከተ ጥያቄ በማያስነሳ መንገድ ተግባራዊ ማድረግ ይችል ዘንድ ከአዲሶቹ የጠቅላይ ፍርድ ቤት አመራሮች ጋር በተደረገ ምክክር በጠቅላይ ፍርድ ቤት ስር መልሶ እንዲቋቋምና ስራውን እንዲሠራ ተደርጓል፡፡

3.2  የሲቪል ማህበረሰብ የስራ ቡድን

አማካሪ ጉባኤው ያቋቋመው የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች የሕግ ማዕቀፍ የሥራ ቡድን በሥራ ላይ የነበረዉን የበጐ አድራጐቶችና የማህበራት አዋጅ ቁጥር 621/2001” ለማሻሻል የሚያስችል ፈጣን 

የዳሰሳ ጥናት በማድረግ የሕግና ተቋማዊ የማማሻሻያ ምክረ-ሀሳቦችን እንዲያቀርብ ኃላፊነት ተጥሎበታል፡፡ የሲቪል ማህበረሰብ የስራ ቡድን አባላት ባብዛኛዉ ከሲቪል ማህበረሰብ ዘርፍ የተዉጣጡ ሲሆን የሕግ ባለሙያዋችን፣ሙሁራን፣የሲቪል ማህበረሰብ መሪዋች እንዲሁም ዓለም አቀፍ የሰብዓዊ መብት 

ተቋማት የተካተቱበት ነዉ፡፡

የሲቪል ማህበረሰብ ሕግ ማሻሻያ መርሀግብር አማካሪ ጉባዔዉ ከዴሞክራሲና ሰብዓዊ መብት ጋር ተያያዥ የሆኑ ኃላፊነቶቹን ለመወጣት ዓይነተኛ ሚና የሚጫወት በመሆኑ ከፍተኛ ትኩረት ተሰጥቶ 

ተሰርቶበታል፡፡የስራ ቡድኑ የአዋጁን አተገባበርና ተያያዥ ጉዳዮችን የሚዳስስ ጥናት አካሂዶ፤ በጥናቱ ግኝት መሠረት ባቀረበው ምክረ ሃሳብ አዲስ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ሕግ ረቂቅ ተዘጋጀቶ ለህዝብ 

ተወካዮች ምክር ቤት ቀርቦ አዋጅ ቁጥር 1113/2011 ሆኖ ፀድቋል ፡፡ በዚህ ሂደት የጥናት ቡድኑ በመላው ሃገሪቱ የተለያዩ ባለድርሻ አካላትን ያወያየ ሲሆን ሕጉ የመደራጀት መብትን የተመለከቱ ዓለም ዓቀፍና አህጉራዊ፣ እንዲሁም ሕገ መንግስታዊ መርሆዎችን ባገናዘበ 

መልኩ ተዘጋጅቷል፡፡ 

የተከናወኑ ስራዋች 

ቀን

ተግባ

ሂደት I – የዳሰሳ ጥናት/ሪፖርት

የስራ ቡድኑ የዳሰሳ ጥናት ጀመረ

ሰኔ 25.2010

የስራ ቡድኑ

የዳሰሳ ጥናት ሪፖርት ለአማካሪ ጉባዔዉ ገቢ ሆነ

ነሀሴ22.2010 

የስራቡድኑ፣ፅ/ቤቱ

አማካሪ ጉባዔዉ ሪፖርቱን የገመገመበትና ቀጣይ ሂደቶችን አጸደቀ

ነሀሴ25.2010 

ጉባኤዉና ፅ/ቤቱ

ሂደት II –  ማርቀቅ

የሚመለከታቸዉ አካላት ዉይይት ከሲቪል ማህበረሰብ ተቆጣጣሪ ኤጀንሲ ጋር
ተደርጓል፡፡

ህዳር. 2011

የስራ
ቡድኑ፣ፅ/ቤቱ

በረቂቅ አዋጁ ላይ በዘጠኙ ክልሎችና በሁለቱ ከተማ አስተዳደሮች የህዝብ ዉይይት
ተደርጓል፡፡

ነሀሴ27-
ጳጉሜ5.2010

.
የስራቡድኑ፣ፅ/ቤቱ

ረቂቅ የሲቪል ማህበራት አዋጅ ለአማካሪ ጉባዔዉ ገቢ ሆኖአል፡፡

አማካሪ ጉባኤዉ ረቂቅ አዋጁን ገምግሞ ትችቶችንና በየመፍተሄ ሃሳቦችን
በመጨመር ገቢ አደረገ::

ታህሳስ 2011

አማካሪ ጉባዔዉ

ሂደት III –  ማዉጣት ሂደቱን መደገፍ

ረቂቅ ጉ ለህዝብ ተወካዮች ም/ቤት ለዉይይት ቀረበ::

ጥር17. 2011

የስራ ቡድኑ

አንግሊዘኛዉ ትርጓሜ ከአማርኛዉ ጋር ተመሳሳይ መሆኑን ለማረጋገጥ ግምገማ
ተደርጓል
::

መጋቢት6-
9.2011

የስራ ቡድኑና,
የሲቪል ማህበራት
ኤጀንሲ

የሲቪል ማህበራት አዋጅ ቁጥር 1113/2011 ፀድቆ የሲቪል ማህበር ተቋማት ኤጀንሲ
ተመሰረተ
::

መጋቢት3.
2011

የህዝብ ተወካዮች
ም/ቤት

ሂደት IV – አፈፃፀም፣ድጋፍና ግምገማ

የኤጀንሲዉ የአፈፃፀም እቅድ ሰነድ የማዘጋጀት ሂደት ተጠናቋል.::

መጋቢት 16.
2011

የሲቪል ማህበራት
ኤጀንሲና ፅ/ቤቱ

ደንቦችንንና መመሪያዋችን ለማርቀቅ የሚያግዝ የሀገር ዉስጥ ባለሙያ ለ30 ቀነ
ተቀጥሯል::

ሚያዝያ 7.
2011

የሲቪል ማህበር
ተቋማት ኤጀንሲ
.

ደንቡን ለማርቀቅ ለኤጀንሲዉ ድጋፍ ተደርጓል::

ከግንቦት1-
23.2011

ፅ/ቤቱ

በረቂቅ ደንቡ ላይ የምክክር ፎረም ተካሂዷል::.

ግንቦት
8.2011

የሲቪል ማህበራት
ኤጀንሲና ፅ/ቤቱ

ረቂቅ ደንቡ ለጠቅላይ ቃቤ ግ ገቢ ተደርጓል::

ሰኔ13.2011 

የሲቪል ማህበራት
ኤጀንሲና ፅ/ቤቱ

3.3 የፀረ-ሽብር አዋጅ ማሻሻያ የስራ ቡድን

 የሕግና ፍትሕ ጉዳዮች አማካሪ ጉባዔ የፀረ ሽብር አዋጅ የስራ ቡድን ያደራጀ ሲሆን ይህ የስራ ቡድን በስራ ላይ ያለዉን የፀረ-ሽብር አዋጅ ቁጥር 652/2001 ይዘትና አተገባበር በማጥናት ሕጋዊና ተቋማዊ የማሻሻያ ሃሳቦችን በአጭር ጊዜ እንዲያቀርብ ኃላፊነት ተጥሎበታል፡፡ የስራ ቡድኑ አባላት የታወቁ የሽብር ወንጀል ተጠርጣሪዎች ተከላካይ ጠበቆችን፣ የዩኒቨርሲቲ መምህራን፣ የዘርፉ ሙሁራንን እና የጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ የሕግ ማርቀቅ ባለሙያዋችን ያካተተ ነዉ፡፡

በስራ ላይ ያለዉ የፀረ -ሽብር አዋጅ በኢትዮጵያ ለተደረጉ የሰባዊ መብት ጥሰቶች መሰረታዊ ምክንያት ተደርጎ በመወሰዱ የዚህ አዋጅ ማሻሻያ መርሀ-ግብር ከፍተኛ ትኩረት ተሰጥቶታል፡፡ የስራ ቡድኑ የፀረ- ሽብር አዋጁን እና አዋጁ በስራ ላይ የዋለበትን መንገድ የሚገመግም ጥናት አካሄዶ፣ በጥናቱ መስረት የመጨረሻ ረቂቅ አዋጅ ተዘጋጅቷል፡፡ ረቂቅ አዋጁ ቀድሞ ለሰባዊ መብት ጥሰት ምክንያት የነበረዉን ልዩ የምርመራ ሂደት በማስቀረት በመደበኛዉ የወንጀል ሕገ ምርመራ ሂደት እንዲሆን ከማድረጉም ባሻገር በሽብርተኝነት በመፈረጅ ሂደት ዉስጥ ሊደረጉ የሚገቡ ቅድመ ሁኔታዋችን በጥልቀት አካቷል፡፡በጥናቱ ሂደት የሥራ ቡድኑ ተከታታይ የባለድርሻ አካላት የውይይት መድረኮችን አካሂዷል፡፡

የተከናወኑ ስራዋች

ቀን

ተግባ

ሂደት I – የዳሰሳ ጥናት/ሪፖርት

የስራ ቡድኑ የዳሰሳ ጥናት ማድረግ ጀመረ

ሰኔ, 2010

የስራ ቡድኑ

በዳሰሳ ጥናቱ ላይ ከዳኞች፣ /ህጎችና ጠበቆች ጋር የሚመለከታቸዉ አካላት ዉይይት ተደርጓል

……

የስራ ቡድኑና /ቤት

ከፖለቲካ ፓርቲዋችና የፖለቲካ አንቂዎች ጋር የህዝብ ዉይይት ተደርጓል
የዳሰሳ ጥናቱ ሪፖርት ለአማካሪ ጉባዔዉ ገቢ ሆኗል

………

የስራ ቡድኑና /ቤት

ሀምሌ20
10

የስራ
ቡድኑና
/ቤት

ሂደት II – ሕግ ማርቀቅ

የሕግና ፍትሕ ጉዳዮች አማካሪ ጉባዔ መደበኛ ስብሰባ በፀረ-ሽብር ሕጉ ረቂቅ ላይ ዉይይት አካሂዷል

ኅዳር 28
2011

ከፖለቲካ ፓርቲዋች፣ ከመገናኛ ብዙሃን ተቋማት እና ሌሎች የመንግስት ተቋማት ጋር የአንድ ቀን
ህዝባዊ ዉይይት በአዲስ አበባ ተካሂዷል፡፡

የካቲት21
2011

/ቤቱና የስራ ቡድኑ

ከሰብዓዊ መብት የሕግ ባለሙያዎች፣ ከሰብዓዊ መብት ተቋማት፣ ከቀይ መስቀል ማህበር እና በዉጭ
ሀገር ከሚማሩ የሰብዓዊ መብት ተማሪዎች በረቂቁ ላይ ትችት ተቀብሏል
ረቂቅ የፀረ -ሽብር አዋጁን ለጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ አስረክቧል

….
….

/ቤቱ.
/ቤቱና
አማካሪ
ጉባዔዉ

ሂደትIII – የሕግ ማዉጣት ሂደቱን መደገፍ

ረቂቅ ሽብርተኝነትመከላከልና መቆጣጠር አዋጁ ወደ እንግሊዝኛ ተተርጉሟል

መጋ24
2011

/ቤቱ

ረቂቁን በማጥራት ሂደት ለጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ ድጋፍ አድርጓል

ሚያ 11,
2011

የስራ
ቡድኑ/.ቤቱ

ረቂቅ ሕጉን በማቅረብ ሂደት ላይ ለጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ ድጋፍ አድርጓል

ግን 11
2011

የስራ ቡድኑ/.
ቤቱ

ረቂቅ ሕጉን ለህዝብ ተወካዮች /ቤት በማቅረብ ሂደት ላይ ለጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ ድጋፍ አድርጓል

 

ሰኔ 11 2011   

 

የስራ ቡድኑ/ፅቤቱ

 3.4  የሚድያ ህግ የስራ ቡድን         ቀን       

ሕግና ፍትሕ ጉዳዮች አማካሪ ጉባዔ የመገናኛ ብዙሃን ሕግ የስራ ቡድን በነሀሴ 2011 / ያቋቋመ ሲሆን ይህ የስራ ቡድን በኢትዮጵያ የመገናኛ ብዙሃን ሕግ ላይ ሕጋዊና ተቋማዊ ጥናት በማድረግ የሚድያ ዘርፉ ዉስጥ ስር-ነቀል ሽግግር ሊያመጣ የሚያስችል ምክረ ሀሳብ እንዲያቀርብ ኃላፊነት ተጥሎበታል፡፡ የስራ ቡድኑ በዋናነት የየመገናኛ ብዙሃን፣ የመረጃ ነፃነት፣ የብሮድካስት፣የኮምፒተር ወንጀሎችና ሌሎች ሀሳብን በነፃ ከመግለፅ ጋር የተያያዙ ሕጎች ያለባቸዉን ክፍተት በመገምገም ምክረ ሀሳብ የማቅረብ ኃለፊነት ተጥሎበታል፡፡በጥናት ላይ የተመሠረተ ምክረ ሀሳብ ከማቅረብ ባሻገር ተደራሽና የጎለበተ የመገናኛ ብዙሃን ዘርፍ የሚፈጥሩ የመገናኛ ብዙሃን ሕጎች እንዲያረቅ ኃላፊነት ተሰጥቶታል፡፡ይህ የስራ ቡድን ከሕግ ባለሙያዎች፣ጋዜጠኞች፣ የመገናኛ ብዙሃን ባለቤቶች እና የፆታ ባለሙያዋች የተዉጣጡ አባላትን በማካተት የተቋቋመ ቡድን ነዉ፡፡ የመገናኛ ብዙሃን ሕግ የስራ ቡድን አማካሪ ጉባዔዉ በመጀመሪያ ካቋቋማቸዉ የስራ ቡድኖች መካከል አንዱ ቢሆንም የመገናኛ ብዙሃን ዘርፉ በሚያጋጥሙት ሕጋዊና ተግባራዊ ተግዳሮቶች እንዲሁም በጉዳዩ ስፋትና ጥልቀት ምክንያት የተጠበቀዉን ያህል መሄድ አልቻለም፡፡ሀሳብን በነፃነት የመግለፅና የመገናኛ ብዙሃን ነፃነት በኢትዮጵያ ከዓለም በጣም ዝቅተኛ ከሚባሉት ሀገራት መካከል ሲሆን .. 2018 በተካሄደዉ የድንበር የለሽ ሪፖርተሮች ሪፖርት ከጠቅላላ 180 ሀገሮች 150 ደረጃ ላይ ተቀምጣለች፡፡ይህን ተከትሎም የኢትዮጵያ የመገናኛ ብዙሃን ዘርፍ በአፍሪካ ደረጃም ቢሆን ዝቅተኛ ሲሆን ያሉት አብዛኞቹ ሚድያዎችም በመንግስት ቁጥጥር ስር ናቸዉ፡፡ ችግሩን ከስሩ ለመፍታት የስራ ቡድኑ የመገናኛ ብዙሃን ዘርፉን ያቀጨጩ ሕጋዊ፣ አስተዳደራዊና ፖለቲካዊ ርምጃዋች ለማጥናት ከፍተኛ ሰነዶችን መርምሯል፡፡ የስራ ቡድኑ የማሻሻያ ትኩረቱን እንዳስፈላጊነታቸዉ በቅደም ተከተል በመገናኛ ብዙሃን፣ በብሮድካስት፣ በመረጃ ነፃነት እና የኮምፒተር ወንጀል ሕጎች ላይ አድርጓ እየሰራ ይገኛል፡፡

የተሰሩ ስራዋች

ቀን

ተግባር

ሂደት I – የዳሰሳ ጥናት/ሪፖርት

የዳሰሳ ጥናት ሪፖርት ለአማካሪ ጉባዔዉ ቀርቧል፡፡

ጥቅምት 26-
28.2011

የስራቡድኑና /ቤቱ

የመጀመሪያ የዳሰሳ ጥናት ሪፖርት ለአማካሪ ጉባዔዉ ገቢ ሆኗል፡፡
በረቂቅ የዳሰሳ ጥናቱ ላይ ሁለት የባለድርሻ አካላት ዉይይቶች ተካሂዷል፡፡

ኅዳ29.2011
የካቲት8.2011

የስራቡድኑና /ቤቱ
የስራቡድኑና /ቤቱ

በረቂቅ ሪፖርቱ ላይ በካፒታል ሆቴል 2ተኛ የባለድርሻ አካላት ዉይይት ተካሂዷል፡፡

ኅዳር 29.2011

የስራቡድኑና /ቤቱ

የስራ ቡድኑ መነሻና መዳረሻ፤ የመገናኛ ብዙሃን ሚና ለዴሞክራሲ ግንባታ” የተሰኘ ኮንፍረንስ
በሂልተን ሆቴል አዘጋጅቶ አቅርቧል፡፡

የካቲት 21 2011

የስራ ቡድኑ

የመነሻ ግኝቶችን ለማብራራትና ግብዐት ለመሰብሰብ ከተለያዩ የመገናኛ ብዙሃን ባለሙያዋች ጋር
ዉይይት ተደርጓል ፡፡

መጋቢት7.2011

የስራ ቡድኑ/.ቤቱ

ሁለተኛዉ የዳሰሳ ጥናት ሪፖርት ለአማካሪ ጉባዐዔዉ ገቢ ሆኗ፡፡

መጋቢት21.2011

.ቤቱ

አማካሪ ጉባዔዉ ሙሉ የዳሰሳ ጥናትና የፀደቀ የፖሊሲ የመፍትሄ አቅጣጫ እንዲኖር ሀሳብ
አቅርቧል፡፡

መጋቢት27.2011

የስራ ቡድኑ/.ቤቱ

ሂደት II –ሕግ ማርቀቅ

የካቲት13.2011

የስራ ቡድኑ

የተለያዩ አሥተያየቶች ከአማካሪ ጉባዔዉና ከህዝብ ዉይይቶች እየመጡ በነበረበት ተመሳሳይ ጊዜ የማርቀቅ ስራዉን ጀምሯል፡:
የመገናኛ ብዙሃን፣ የኮምፒተር ወንጀል እና መረጃ የማግኘት መብት ሕግን የማርቀቅ ሂደቱን ለመደገፍ ሦስት የሀገር ዉሥጥ ባለሙያዋች 30 ቀን ተቀጥረዋል፡፡
በረቂቅ የመገናኛ ብዙሃን ሕጉ ላይ ወሳኝ ነጥቦች ላይ ለመወያየት በአዲስ አበባ
ዩኚቨርሲቲ ሰብዓዊ መብቶች ማዕከል የባለሙያዋችና የሚመለከታቸዉ አካላት ስብሰባተደርጓል፡:
ረቂቅ የመገናኛ ብዙሃን ሕጉ ለአማካሪ ጉባዔዉ ደርሶት ተወያይቶ አቅጣጫዋችንአስቀምጧል፡:
የመጀመሪያ ደረጃ የማርቀቅ ሂደቱ ተጠናቀቀ፡:
40 ከሚሆኑ ከመገናኛ ብዙሃን አካላት ተዋናዮች ጋር የባለድርሻ አካላት ዉይይትተደርጓል፡፡
ከሲቪል ማህበረሰብ አባላትና ከህዝብ ጋር በረቂቅ የሚድያ ሕጉ ላይ የህዝብ ዉይይት ተካሂዷል፡:
በረቂቅ የሚድያ ሕጉ ላይ ከብሮድካስትና ህትመት ሚድያዋች ጋር የህዝብ ዉይይትተካሂዷል፡:
በረቂቅ የሚድያ ሕጉ ላይ በመቀሌ፣በባህርዳር፣በሐዋሳና በድሬ ዳዋ የህዝብ ዉይይት
ተካሂዷል፡:
የሲቪል ማህበረሰብ አካላትንና የፖለቲካ ፓርቲዋች ጨምሮ ሰፊ የህዝብ ዉይይት
ተደርጓል፡፡
የመጨረሻ የባለድርሻ አካላት ዉይይት 40 ከሚሆኑ የሚድያ ኢንዱስትሪ ተዋናዮች ጋርተደርጓል፡:

ረቂቅ የሚድያ ሕጉ ለዓለም ዓቀፍ ገምጋሚ ባለሙያዋች ወደ እንግሊዝኛ እየተተረጎመነዉ፡:የማርቀቅ ሂደቱ እንደቀጠለ ነዉ፡:

ግንቦት7.2011
ሚያዝያ26.2011
ግንቦት9-23.2011
ግንቦት25.2011
ግንቦት30-
ሰኔ2.2011
ሰኔ15.2011
ሰኔ22.2011
ሰኔ28-
ሰኔ30.2011
ሀምሌ8.2011
ሀምሌ12-
13.2011

/ቤቱ
የስራ ቡድኑ
ጉባዔዉ፣የስራ
ቡድኑ፣ፅ/ቤቱ
የስራ ቡድኑ
የስራቡድኑና /ቤቱ
የስራቡድኑና /ቤቱ
የስራቡድኑና /ቤቱ
የስራ ቡድኑና /ቤቱ
የስራ ቡድኑና /ቤቱ
የስራ ቡድኑና /ቤቱ

3.5  የዴሞክራሲ ተቋማት የስራ ቡድን 

በዘርፉ ከፍተኛ ልምድ ያላቸዉ 12 አባላትን ያካተተዉ የዴሞክራሲ ተቋማት የስራ ቡድን በምርጫሕጎችና ተቋማት፣ በሰብዓዊ መብት ኮሚሽን፣በህዝብ እምባ ጠባቂ ተቋም፣በፌዴሬሽን /ቤትና በሕገ-መንግስት ጉዳዮች አማካሪ ጉባዔ ላይ ህጋዊና ተቋማዊ የዳሰሳ ጥናት በማድረግ ምክረ ሀሳቦች እንዲያቀርብ ስልጣን ተሰጥቶታል፡፡የስራ ቡድኑ ስልጣን ሰፊ ቢሆንም እንኳን መጭዉን 2012 ሀገራዊ ምርጫ ተከትሎ በአማካሪ ጉባዔዉ በተሰጠዉ አቅጣጫ መሰረት ምርጫ ነክ በሆኑ ሕጎች ላይ ትኩረት አድርጎ እየሰራ ይገኛል፡፡ ስለሆነም የስራ ቡድኑ ጤናማ የምርጫ ሥርዓት ለመፍጠር የሚያስችሉ ማለትም የኢትዮጲያን ምርጫ ቦርድን መልሶ ማቋቋም፣ የምርጫ ቁጥጥር፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች የሥነ-ምግባር ደንብ እና የፖለቲካፓርቲዋች ምዝገባ ሕጎች ዙሪያ እየሰራ ይገኛል፡፡ቅድሚያ ከተሰጣቸዉ ምርጫ ነክ ሕግ ማሻሻያዋች አኳያ የስራ ቡድኑ መቀመጫ ወደ የኢትዮጲያ ምርጫ ቦርድ የተዛወረ ቢሆንም የማሻሻያ ሂደቱ ከአማካሪ ጉባዔዉ ጋር የተቆራኘ ነዉ፡፡

የተሰሩ ስራዋች

ቀን

ተግባር

ሂደት I – የዳሰሳ ጥናት/ሪፖርት

ይህ የስራ ቡድን በምርጫ ሕግ ቁጥር532/2000፣በፖለቲካ ፓርቲዎች የሥነምግባር ደንብና የፖለቲካ
ፓርቲዋች ምዝገባ አዋጅ ላይ ጥናት በማድረግ ለአማካሪ ጉባዔዉ አስገብቷል
ከሚመለከታቸዉ የብሄራዊ ምርጫ ቦርድ አካላት ጋር በብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ዋና /ቤት ዉይይት
አካሂዷል፡፡

ጥቅምት6.2011

የስራ ቡድኑ
የስራ ቡድኑና /ቤቱ

በዳሰሳ ጥናቱ ላይ ከፖለቲካ ፓርቲዋችና ሌሎች የሚመለከታቸዉ አካላት ጋር በኢንተርኮንቲነንታል
ሆቴል ዉይይት ተደርጓል፡፡

ኅዳር13.2011

የስራ ቡድኑና /ቤቱ

ሂደት II ሕግ ማርቀቅ

የሕግ ማርቀቅ ስራዉ ተጀምሯል፡፡
የኢትጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድን መልሶ ለማደራጀት በወጣዉ ረቂቅ አዋጅ ላይ ከፖለቲካ ፓርቲዋችና
ሌሎች አካላት ጋር በእሊሊ ሆቴል ዉይይት አካሂዷል፡፡
በፖለቲካ ፓርቲዋች ምዝገባ አዋጅ፣ በፖለቲካ ፓርቲዋች የሥነ-ምግባር ደንብና በምርጫ ሥርዓት ላይ
በቀረቡ የዳሰሳ ጥናቶች ዙርያ ከፖለቲካ ፓርቲዋችና ከማህበረሰብ አንቂዋች ጋር ዉይይት ተደርጓል፡፡
ከዓለም አቀፍ የምርጫ ባለሙያዋች ጋር በማሪዮት ሆቴል ዉይይት ተደርጓል፡፡
የሙሉ ሰዓት አማካሪ ተቀጥሯል፡፡

ታኅሳስ
10.2011
ጥር1.2011

የስራ ቡድኑ
የስራ ቡድኑና /ቤቱ
የስራ ቡድኑና /ቤቱ
የስራ ቡድኑና /ቤቱ

ሂደት III – የሕግ ማዉጣት ሂደቱን መደገፍ

የስራ ቡድኑ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድን መልሶ ለማቋቋም የወጣዉን ረቂቅ አዋጅ ለህዝብ
ተወካዮች እና ለሚኒስትሮች /ቤት በማቅረብ ሂደት ዉስጥ በም/ቤቶች ፊት በመቅረብ ረቂቅ አዋጁን
ተከላክሏል፡፡


 


 3.6  የሕግ አወጣጥ ሂደትና የአስተዳደር ሕግ የስራ ቡድን

 

የሕግ አወጣጥ ሂደትና የአስተዳደር ሕግ የስራ ቡድን የዓለም ባንክ የቁጥጥር ፖሊሲና የአፈፃፀም ክለሳ(ቁፖአክ)” በሚል ርዕስ ባካሄደዉ ጥናት ባቀረበዉ ምክረ ሀሳብ መሰረት ነዉ፡፡የቁፖአክ ዓላማ የቁጥጥር ፖሊሲዋች፣ተቋማትና የአፈፃፀም ዘዴዋች በመለየትና በመከለስ የተሻሉ የአመራር ፖሊሲዎችን እዉን ማድረግ እንደሚቻል ማሳየት ነዉ፡፡አንደኛዉ የጥናቱ ግኝት በሕግ አወጣጥና ትግበራ ሂደት የሚታዩ ሕጎችን በንዑስ ሕጎች በየፈርጁ ከፋፍሎ በማዉጣትና በመፈፀም ሂደት ዉስጥ ያለዉን ክፍተት ማሳየት ነዉ፡፡በዚህም መሰረት ጥናቱ የተሸለ የአስተዳደራዊ ሕግ አወጣጥና አፈፃፀም ቅድመ ሁኔታዎችና ሥነ-ሥርዓቶች በተግባር ማዋል የሚያስችለዉን የአስተዳደር ሥርዓት ኮድ አስፈላጊነት በምክረ-ሀሳብነት አቅርቧል፡፡ በተጨማሪም የዚህ ንዑስመርሓግብር ዓላማ ሕጎቻችን ህዝብ አሳታፊና ዴሞክራሲያዊ በሆነ መንገድ በይዘትም ይሁን በመሠረት ጥራታቸዉን የጠበቁ ሆነዉ እንዲወጡ ማድረግ ነዉ፡፡

በዚህም መሰረት የስራ ቡድኑ ያለዉን ረቂቅ የአስተዳደር ሥነ-ሥርዓት አዋጅ በማጥናት ጥራቱን እንዲያሻሽል ኃላፊነት ተጥሎበታል፡፡ በተጨማሪም የሕግ አወጣጥ ሂደቶችን በመገምገም የኢትዮጵያ ዋና ዋና ሕጎች ከሕገ-መንግስቱና ከዓለም-ዓቀፍ ስምምነቶች ጋር የተጣጣሙ እንዲሆኑ የሚያስችል የሕግ አወጣጥ መንገዶችን የማምጣት ኃላፊነት ተጥሎበታል፡፡ በተለያዩ አካላት የተዘጋጁ ረቂቅ የአስተዳደር ሥነ-ሥርዓት ሕጎች መኖራቸዉን ተከትሎ የስራ ቡድኑ ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ 2009 / ያዘጋጀዉን ረቂቅ የአስተዳደር አዋጅ አሻሽሎ እንዲያቀርብ ተወስኗል፡፡

 

የተሰሩ ስራዋች

ቀን

ተግባር

ሂደት I –የዳሰሳ ጥናት/ሪፖርት

የስራ ቡድኑ የትግበራ ዕቅድ አዘጋጅቶ ለአማካሪ ጉባኤዉ አስረክቧል፡፡

ጥቅምት22.2011

የስራ ቡድኑ

ሂደት II –ህግ ማርቀቅ

የነበረዉን የፌደራል የአስተዳደር ሕግ አዋጅ እንደገና አርቅቋል፡፡
በረቂቁ ላይ ዉይይት ተካሂዷል፡፡
አማካሪ ጉባዔዉ በረቂቁ ላይ ተወያይቷል፡፡

ከጥር-
ሚያዝያ.2011
ከመጋቢት28-
30.2011
ሰኔ14.2011

የስራ ቡድኑ
የስራ ቡድኑ
የስራ ቡድኑ

3.7  የወንጀል ፍትሕ ሥርዓት የስራ ቡድን

 

የሕግና ፍትሕ ጉዳዮች አማካሪ ጉባዔ የወንጀል ፍትሕ ሥርዓት የስራ ቡድንን አጠቃላይ የኢትዮጵያን የወንጀል ፍትሕ ሥርዓት በማጥናት የማሻሻያ ምክረ ሀሳብ እንዲያቀርብ አቋቁሟል፡፡የስራ ቡድኑ 21 የዘርፉ ባለሙያዋችን በማካተት ነሃሴ 9 ቀን 2011 . የተቋቋመ ሲሆን በተመሳሳይ ቀን ስራዉን ጀምሯል፡፡ የስራ ቡድኑ ከምስረታዉ ጀምሮ በወንጀል ፍትሕ ሥርዓት ዙሪያ ጥቅል የመነሻ ጥናት ሲያዘጋጅ ቆይቷል፡፡የጥናት ቡድኑ በኢትዮጵያ የወንጀል የፍትሕ ሥርዓት ሁኔታ ላይ ጥናቱን ከታህሳስ መጀመሪያ እስከግንቦት መጨረሻ ድረስ እንዲጨርስ ይጠበቅ የነበረ ቢሆንም ከአማካሪ ጉባዔዉና ከጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ጋር በመነጋገር በስራ ላይ ባለዉ የማረሚያ ቤት አዋጅ እና በወንጀለኛ መቅጫ ሥነ-ሥርዓትና ማስረጃ አዋጅ ላይ ትኩረቱን አድርጎ እንዲሰራ ተወስኗል፡፡በዚህም መሰረት የተመረጡ የስራ ቡድኑ አባላት የፌዴራል ማረሚያ ቤቶች ኮሚሽን ያዘጋጀዉን ረቂቅ አዋጅ አሻሽሎ እንዲያቀርብ ተመድቧል፡፡በፌዴራል ማረሚያ ቤቶች ኮሚሽን የተዘጋጀዉ ረቂቅ አዋጅ በተፈፃሚነት ወሰንና የሰብዓዊ መብት ድንጋጌዋችን ከማካተት አንፃር ሰፊ ለዉጥ ተደርጎበታል፡፡ የስራ ቡድኑ ረቂቅ አዋጁን ካሻሻለ በኋላ ከከፍተኛ የፌዴራል ማረሚያ ቤቶች ኮሚሽን ከፍተኛ ባለስልጣናት ጋር ዉይይት ተደርጎ የመጨረሻዉ ረቂቅ ምን መምሰል እንዳለበት መግባባት ላይ ተደርሷል፡፡

 የወንጀል ሥነ-ሥርዓትና ማስረጃ ሕጉን በተመለከተ የስራ-ቡድኑ ረቂቅ የወንጀለኛ ሥነ-ሥርኣት ሕጉን የካቲት 24 ቀን 2011 . ተቀብሎ በረቂቁ ላይ ዉይይት ተካሂዷል፡፡ ረቂቅ የወንጀል ሥነ-ሥርዓትና ማስረጃ አዋጁ በፍጥነት እንዲጠናቀቅ መወሰኑን ተከትሎ የስራ ቡድኑ ሌሎች ኃላፊነቶችን በመተዉ በዚህ ረቂቅ ላይ ሙሉ ጊዜዉን ሰጥቶ እየሰራ ይገኛል፡፡

የተሰሩ ስራዋች

ቀን

ተግባር

ሂደትI – የዳሰሳ ጥናት/ሪፖርት

 

የስራ ቡድኑ በአግባቡ ተቋቁሞ ይፋ ሆኗል፡፡
የሙሉ ጊዜ አማካሪ ተቀጥሯል፡፡
የመነሻ ሪፖርት ተዘጋጅቶ ለአማካሪ ጉባዔዉ ገቢ ሆኗል፡፡
የስራ ቡድኑ የዳሰሳ ጥናት ሪፖርት አስረክቧል፡፡
ያለዉን ረቂቅ ለማሻሻል ዉሳኔ ተላልፏል፡፡

ነሀሴ11.2011
ጥቅምት23.2011

የስራ ቡድኑ
የስራ ቡድኑ
አማካሪ ጉባዔዉ

ሂደት II –ሕግ ማርቀቅ

በወንጀለኛ መቅጫ ሥነ-ሥርዓት ሕጉ ላይ ስራ ተጀምሯል፡፡

መጋቢት7.2011

የስራ ቡድኑ የፌዴራል ማረሚያ ቤቶች ረቂቅ አዋጆች ለአማካሪ ጉባዔዉና ለፅ/ቤቱ አስረክቧል፡፡
አማካሪ ጉባዔዉ ረቂቅ የፌዴራል ማረምያ ቤቶች አዋጁን ለጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ አስረክቧል፡፡
ረቂቅ የፌዴራል ማረምያ ቤቶች አዋጁ ወደ እንግሊዝኛ ተተርጉሟል፡፡
የስራ ቡድኑ ረቂቅ የወንጀለኛ ሥነ-ሥርዓትና የማስረጃ አዋጁን ለአማካሪ ጉባዔዉ አስረክቧል፡፡
በረቂቅ የወንጀለኛ መቅጫ ሥነ-ሥርዓት ሕጉ ላይ አማካሪ ጉባዔዉና የስራ ቡድኑ የጋራ ምክክር
አካሂደዋል፡፡
የመጨረሻዉ አማርኛ ረቂቅ የወንጀለኛ ሥነ-ሥርዓትና የማስረጃ አዋጅ ለጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ ገቢ
ሆኗል፡፡
የመጨረሻዉ እንግሊዝኛ ረቂቅ የወንጀለኛ ሥነ-ሥርዓትና የማስረጃ አዋጅ ለጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ ገቢ
ሆኗል፡፡

መጋቢት9.2011
መጋቢት23.2011
ሚያዝያ2.2011
ሚያዝያ4-
6.2011
ሰኔ15.2011
________

የስራ ቡድኑ
የስራ ቡድኑና
አማካሪ ጉባዔዉ
/ቤቱ
የስራ ቡድኑና
አማካሪ ጉባዔዉ
/ቤቱ
የስራ ቡድኑ፣
አማካሪ ጉባዔዉ
/ቤቱ
የስራ ቡድኑ
የስራ ቡድኑና
አማካሪ ጉባዔዉ

  3.8  የንግድና የፍትሐብሔር ሕግ የስራ ቡድን

የሕግና ፍትሕ ጉዳዮች አማካሪ ጉባዔ በኢትዮጵያ የንግድ እንዲሁም የፍትሐብሔር ሕግ ዙርያ ያሉ ማነቆዎችን በመለየት የመፍትሄ ሀሳብ እንዲያቀርብ በነሀሴ 2010 . የንግድና ፍትሐብሔር ሕግ የስራ ቡድን ያቋቋመ ሲሆን የስራ ቡድኑ አስር የትርፍ ሰዓት በጎ ፈቃደኛ አባላት ብቻ ነው ያሉት፡፡ ለረጅም ጊዜ በሥራ ላይ የቆየውን የንግድ ሕግ ለማሻሻል ከዚህ ቀደም የተጀመረው ሥራ በቅርቡ ተጠናቆ ረቂቅ የንግድ ሕጉ የተዘጋጀ ቢሆንም ይህን ዓይነት ሕግ ለሃገሪቱ ያለውን ኢኮኖሚያዊ ፋይዳ፣ በኮድ መልክ የሚዘጋጁ ሕጐች ሊኖራቸው የሚገባውን ዘመን ተሻጋሪ ባህሪና የንግድ እንቅስቃሴ በአሁኑ ወቅት ከመቼውም ጊዜ በላይ ድንበር ተሻጋሪ እየሆነ መምጣቱን ከግምት ባስገባ መልኩ ረቂቁን መከለስና ማሻሻል አስፈላጊ ሆኖ ተገኝቷል፡፡