መመሪያ ቁጥር 24/2010መመሪያ  ቁጥር 24/2010

የፌዴራል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ የሕግና ፍትሕ ጉዳዮች አማካሪ ጉባኤ ማቋቋሚያ መመሪያ

ማናቸውም የሕዝብ አስተዳደር ስራ፤በሕግ የበላይነትና ዴሞክራሲያዊ መርሆች  ላይ ሊመሰረት እና በሕግመንግስቱ እውቅና ያገኙ መሰረታዊ መብቶችን ሊያከብር የሚገባው በመሆኑ፤ 

የፍትሕና የዴሞክራሲ ተቋማትን የማሻሻል ሂደት ህዝብንና ባለሙያዎችን ባሳተፈ መልኩ ተግበራዊ ማድረግ አስፈላጊ በመሆኑ የፍትህና ዴሞክራሲ ተቋማት አገልግሎት ውጤታማነትና የሕዝብ ፍላጎትን በማርካት ረገድ ያሉትን ችግሮች በወቅቱ በመለየት፤ ተቋማዊ የለውጥ    ፕሮግራሞችን መተግበር አስፈሊጊ በመሆኑ፤ 

የለውጥ ፕሮግራሞችን ለመንደፍና አፈጻጸማቸውን ለመገምገም፤ መረጃንና፤ ልምድና አሳታፊና ሳይንሳዊ በሆነ መንገድ መሰብሰብና መተንተን አስፈላጊ በመሆኑ፤ የፌደራል ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ በአዋጅ ቁጥር 943/2008 አንቀፅ 8/2// መሰረት ይህንን መመሪያ አዉጥቷል፡፡

ክፍል - አንድ

ጠቅላላ ድንጋጌ

1. አጭር ርዕስ

ይህ     መመሪያ  “በፌዴራል   ጠቅላይ   ዐቃቤ      ሕግ    የሕግና    ፍትሕ    ጉዳዮች   አማካሪ   ጉባኤ ማቋቋሚያ መመሪያ ቁጥር 24/2010" ተብሎ ሊጠቀስ ይችላል።

2. ትርጓሜ

1.  " የሕግና  ፍትሕ  ጉዳዮች አማካሪ ጉባኤ" ማለት በዚህ መመሪያ አንቀፅ 3 መሰረት የተቋቋመው ጉባኤ ነው፡፡

2. "ፌዴራል ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ" ማለት በአዋጅ ቁጥር 943/2008 አንቀፅ 3 መሰረት የተቋቋመው ተቋም ነው፡፡ 

3. "ጠቅላይ  ዐቃቤ  ህግማለት  በህዝብ  ተወካዮች  ምክር  ቤት   የተሾመ   የፌደራል ጠቅላይ  አቃቢ ህግ ሀላፊ  ነው፡፡ 

4. ሰው ማለት የተፈጥሮ ሰው ወይም በህግ የሰውነት መብት የተሰጠው አካ ነው፡፡ 

5. ማንኛውም በወንድ ፆታ የተገለፀው አነጋገር ሴትንም ይጨምራል፡፡


ክፍል ሁለት

አደረጃጀት፣ ስልጣንና ተግባር

3. መቋቋም

1.  የሕግና  ፍትሕ  ጉዳዮች አማካሪ ጉባኤ    (ከዚህ በኋላ "ጉባኤ" እየተባለ የሚጠራፌደራል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ስር በዚህ መመሪያ ተቋቁሟል። 

2. የጉባኤው ተጠሪነት   የጠቅላይ አቃቤ ህጉ ነው፡፡4. ዓላማዎች

ጉባኤው የሚከተሉት ዓላማዎች ይኖሩታል፦

1. በሕግና ፍትሕ ጉዳዮች ዙሪያ መረጃና ጥናትን መሰረት በማድረግ  የፌደራል ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ ሙያዊ ምክር መስጠት፤

2.  በፌዴራል  ጠቅላይ  ዐቃቤ  ህግ የሚረቀቁ ህጎች ጥራታቸውን የጠበቁ እንዲሆኑ ተገቢውን እገዛ ማድረግ፤

3.     የህግና    የፍትህ    ስርዐት    ማሻሻያ   ፕሮግራም   ውጤታማ   በሆነ    መንገድ እንዲከናወን አቅጣጫዎችን እና የመፌትሄ ሀሳቦችን ማመንጨት፤

5. ሥልጣንና ተግባራት

ምክር ቤቱ የሚከተሉት ስልጣንና ተግባራት ይኖሩታል፡-

1. በህግና    ፍትህ     ጉዳዮች     ላይ    መሻሻል    ያለባቸውን    ተቋማት፣   አሰራሮችና     ህጎች በሚመለከት ፌዴራል ጠቅላይ ዐቃቤ ህግን ያማክራል፣ የፍትሕና ዴሞክራሲ ተቋማት ፍትሃዊ፣ ቀልጣፋ፣ ውጤታማ፣ ህዝብን የሚያረካ አገልግሎትን እየሰጡ መሆኑን ለመከታተልና  ለመገምገም፤  የክትትልና ግምገማ ማዕቀፍ ያዘጋጃል፤

 2. የክትትልና የግምገማ ማዕቀፍን፣ መረጃና ጥናትን መሰረት በማድረግ የተለያዩ የፍትህና ዴሞክራሲ ተቋማት የሚሰጧቸው አገሌግሎቶች ያለበትን ወቅታዊ ሁኔታና ችግሮችን ይለያል፣ የመፍትሄ ሃሳቦችን እና ረቂቅ ህጎችን የፋዴራል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ያቀርባል፡፡

3. የምክክርና ዉይይት መድረኮች ያዘጋጃል፣ ይመራል፡፡

4. ከዚህ መመሪያ ጋር አባሪ ሆኖ የቀረበውን የምክር ቤቱን የስራ ፕሮግራም ያከናውናል፤እንደ
አስፈላጊነቱም
ያሻሽላል፡፡

6. የጉባኤው አባላት

1.  ጉባኤው አስራ ሶስት አባላት ይኖሩታል፤

2.  የጉባኤው አባላት በዚህ መመሪያ የተሰጣቸውን ሃሊፊነቶች ሲያከናዉኑ፤ ተገዢነታቸው  ለሕሊናቸውና ለሙያቸው ስነ-ምግባራቸው ብቻ ነው፤

3. ማናቸውም የጉባኤው አባል ከተሰጠው  ሃላፊነት    ጋር    የሚጋጭ    የግል ጥቅምና ግንኙነቶች  ካጋጠመው  ሱን   
እንዲገል    ቤቱ  ሊወሰ 

4. የጉባኤው አባላት በፌዴራል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ይመረጣል፤

7. የስራ ዘመን

የምክር ቤቱ አባላት የስራ ዘመን ለሶስት አመት ይሆናል፣ ሆኖም እንደአስፈሊጊነቱ የፌደራል ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ ሀላፊ የስራ  ዘመናቸውን  ሊያዝም 
፡ 

8. የምክር ቤቱ የስብሰባ ሥነ-ሥርዓት

1. ከምክር ቤቱ አባላት ከግማሽ በላይ የሚሆኑት በስብሰባው ላይ  ከተገኙ  ምልዓተ  ጉባኤ ይሆናል፡፡

2.  የምክር  ቤቱ  ውሳኔ  በተቻለ  መጠን  በጋራ  ወይም  በተባበረ  ድምፅ  ይህም  ሳይቻል ሲቀር በአብላጫ ድምጽ ይተላለፋል፤ ሆኖም ድምጽ  እኩል  ለእኩል  እንደሆነ ሰባሳቢው ወሳኝ ድምጽ ይኖረዋል፡፡

3. የዚህ አንቀጽ ንዐስ አንቀጽ ድንጋጌዎች እንደተጠበቁ ሆኖ ምክር ቤቱ የራሱን የስብ 
ሥነ-  ውስጠ 
ደንብ  ሊያወጣ 
ል፡

9. የምክር ቤቱ አሰራር

1. ጉባኤው በጽህፈት ቤቱ የሙሉ ጊዜ ሰራተኞች ይታገዛል።

2. ጉባኤው የተለያዩ የስራ ቡድኖችን  በማቋቋም  መረጃ  የመሰብሰብና  ጥናት  የማካሄድ፣  ረቂቅ ሕጎች የማዘጋጀት የምክክር መድረኮችን የማዘጋጀት አስተያየት የመቀበልና የማደራጀት ስራዎች እንዲከናወኑ ያደርጋል። 

3. ጉባኤው በስራ ቡድኖቹ የሚከናወኑ ጥናቶችና የሚዘጋጁ ረቂቅ ሕጎች ላይ በመወያየት ተጨማሪ መረጃና ጥናት ሲያስፈልግ  የስራ  ቡድኖቹ እነዚህን እንዲያቀርቡለት ማድረግና ላም አስፈላጊውን የስራ መመሪያ ሊሰጥ ይችላል።

10. የጉኤው ጽህፈት ቤት

1. ጉባኤውንና የስራ ቡድኖችን የሚያስተባብርና የሚያግዝ የሕግና ፍትሕ ጉዳዮች ጉባኤ ፅህፈት ቤት (ከዚህ በኋላ "ፅህፈት ቤት" እየተባለ የሚጠራ) በፌዴራል ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ ውስጥ ይደራጃል፡፡

2. ፅህፈት ቤቱ ቋሚ ሰራተኞች የሚኖሩት ሲሆን አስፇሊጊው ግብአትም በፌዴራሌ          ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ ይሟላለታል፣

3. የጽህፈት ቤቱ  ሃላፊና  ምክትል  ሃሊፊ በጠቅሊይ አቃቤ ሕጉ ይመደባል፤ 

4. የጽህፈት ቤቱ አደረጃጀት ከዚህ መመሪያ ጋር አባሪ ሆኖ በቀረበው መሰረት ይሆናል፡፡ ሆኖም  የጽህፈት ቤቱ ሃላፊ ከምክር ቤቱ ሰብሳቢ ጋር በመነጋገር ጽህፈት ቤቱን በተለየ መልኩ ሊያደራጀው ይችላል።

11. የፌዴራል ጠቅላይ ዐቃቤ   ሕግ ሀላፊነት 

የፌዴራል ጠቅላይ ዐቃቢ ሕግ፤

1. ለጉባኤው፣ ለስራ ቡድኖቹ እና የፅህፈት ቤቱ አስፈሊጊውን ድጋፍ ያደርጋል፡፡ የጉባኤውና የስራ ቡድኖች አባላት  ለሚያቀርቡት ነጻ ሙያዊ አገልግሎት እውቅና ይሰጣል።

2. በጉባኤው የሚቀርቡ ረቂቆችንና ምክረ ሃሳቦችን በመንግስት መደበኛ አሰራር መስረት በተቻለው ፍጥነት ውሳኔ ይሰጣል፥ ወይም የሚመለከታቸው የመንግስት አካላት አስቀርቦ ያስወስናል።

ክፍል ሶስት

ልዮልዩ ድንጋጌዎች

12. የተሻሩ ህጎች

ከዚህ መመሪያ ጋር የሚቃረን ማንኛዉም መመሪያ፣ማንዋል እና የአሰራር ልምድ  ይህ መመሪያ ከወጣበት ጊዜ ጀምሮ በዚህ መመሪያ በተሸፈኑ ጉዳዮች ላይ ተፈፃሚነት 
አይኖረ፡፡

13. መመሪያዉ የሚፀናበት ግዜ

ይህ መመሪያ የስራ ሂደቶች ምክር ቤት ቀርቦ ከፀደቀበት ቀን ጀምሮ የፀና ይሆናል፡፡

አዲስ አበባ ቀን 2010 /

ብርሀኑ ፀጋዬ

የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ

ጠቅላይ  ዐቃቤ ህግ

0 Comments

Leave a Comment